ተጨማሪ መረጃ
ሁለት ተጨማሪ የሥራ ቡድኖች በተመካከሩባቸው ምክረ-ሃሳቦች ላይ መግባባት ላይ ደረሱ
ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም
👉በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት
👉በሙስና እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች
ሲመካከሩ የቆዩት እያንዳንዳቸው 500 አባላት ያሏቸው የሥራ ቡድኖች ተጠናቅረው በቀረቡ የአጀንዳ ምክረ-ሀሳቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በተዘጋጁት የቃለ-ጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈረም አረጋግጠዋል።
ምክክር እየተደረገባቸው ከሚገኙ 8 አጀንዳዎች መካከል እነዚህ ሁለት ተመካካሪ ቡድኖች ተጠቃሽ ሲሆኑ በእነዚህ አጀንዳዎች ላይ በተለያዩ የቡድን አደረጃጀቶችና እርከኖች ሲመካከሩ መቆይታቸው የሚታወስ ነው።




