የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የምክክር አጀንዳዎች

የምክክር አጀንዳዎችን ማሰባሰብ፣ ልየታ እና ቀረጻ

የምክክር አጀንዳ

በሀገራዊ ምክክር ሂደት ወሳኝ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ምክክር የሚደረግባቸውን አጀንዳዎች ማሰባሰብ፣ መለየትና መቅረጽ ነው፡፡ ሂደቱን በተመለከተ ሀገራዊ ምክክር በተካሄደባቸው ሀገራት የተለያዩ ተሞክሮዎች ናቸው ያሉት፡፡

በብዙዎቹ በምክክር ባለፉ ሀገራት ምክክር የሚደረግባቸው አጀንዳዎች አስቀድመው ተለይተውና ታውቀው በአጀንዳዎቹ ላይም እነማን እንደሚመካከሩ ተለይተው ሂደቱ የቀጠለበት አግባብ አለ፡፡  አጀንዳዎች አስቀድመው ተወስነው የሚደረግ ሀገራዊ ምክክር በውስን አጀንዳዎች ላይ ብቻ የሚያተኩር ሲሆን ተሳታፊዎቹም ውስን የህብረተሰብ ክፍሎች በአብዛኛውም ሊሂቃንና የፖለቲካ መሪዎች  የሚሆኑበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡

በሌላ አካሄድ ደግሞ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ፣ የመለየትና ቅርጽ የማስያዝ ተግባር የምክክር ሂደቱ አንድ አካል ሆኖ ሊከናወን ይችላል፡፡ ይህ ምክክር ቢደረግባቸው የሚባሉ አጀንዳዎች በሰፊ ተሳትፎና አካታች በሆነ መልኩ የሚለዩበት አካሄድ ሕብረተሰቡንና ባለድሻ አካላትን የምክክሩ ባለቤት እንዲሆኑ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርና የተለያዩ ፍላጎቶችንና ወቅታዊ ጉዳዮችንም በማስተናገድ ሰፊ ምክክሮች እንዲደረጉ እድል የሚሰጥ መሆኑ በጥንካሬ ይወሰዳል፡፡ ሆኖም ግን የምክክር አጀንዳዎቹ በበረከቱ ቁጥር ሰፊ ጊዜና ሀብት ከማስፈለጉ በተጨማሪ መሠረታዊ የሆኑ የልዩነት አጀንዳዎች ላይ በቂ ምክክሮች ሳይደረጉ ቀርተው የሚፈለገው ውጤት ላይ ሳይደረስ እንዳይቀር አካሄዱ ከፍ ያለ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ይታመናል፡፡

በኢትዮጵያ በሂደት ላይ ያለው ምክክር አጀንዳዎቹ አስቀድመው የተወሰኑ ባይሆኑም መርሆዎች ግን ተቀምጠውለታል፡፡ ምክክር እንዲካሄድባቸው የሚቀረጹ አጀንዳዎች እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንዳለባቸው፣ የአለመግባባት መንስዔዎችን በትክክል በሚዲስስ አጀንዳ የሚያተኩሩ እና ጥልቀትና አግባብነት ያላቸው መሆን እንዳለባቸው መርሆዎች ተቀምጠውለታል፡፡

የምክክር አጀንዳዎችን በተመለከተ አንዳንድ ወገኖች እንደ ሀገር የሀሳብ ልዩነት ወይም አለመግባባት የሚታይባቸው አጀንዳዎች ይታወቃሉ፤ አጀንዳ ማሰባሰብና እንደ አዲስ ለመቅረጽ ጥረት ማድረጉ ሂደቱን ከማራዘም ውጭ ፋይዳው ምንድነው ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች በዚህ ብቻም ሳያበቁ አጀንዳዎቹን ለመዘርዘር ጥረት ሲያደርጉም ይስተዋላል፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የአለመግባባት ወይም የሀሳብ ልዩነቶች የሚታይባቸው ጉዳዮች እጅግ መሰረታዊና ሀገራዊ እንደመሆናቸው መጠን በአጀንዳዎቹ ላይ በራሱ አለመግባባቶች ይታያሉ፡፡ ለተወሰነው ሰው አጀንዳ የሆኑ ጉዳዮች ለሌላው አጀንዳ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ አልፎ አልፎም ጉዳዮችን አይነኬ ለማድረግ የሚሞክሩ አመለካከቶችም አሉ፡፡

በእርግጥም ምናልባት በአንዳንድ ሀገራት እንደተደረገው ምክክር የሚደረግባቸው አጀንዳዎች በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ተደንግገው ቢሆን ኖሮ በውስን ሀይል በተቀረጸ አጀንዳ ላይ ምክክር ስለሚደረግበት አግባብነት በርካታ ጥያቄዎችና ተቋውሞች መሰንዘራቸውም አይቀሬ ነበር የሚሉም ወገኖች አሉ፡፡

በምክክር የመግባባት ሂደት በየምዕራፉ መመካከርንና መግባባትን ይጠይቃል፡፡ በዚሁም መሠረት ምክክር በሚካሄድባቸው አጀንዳዎች ላይ መመካከሩና መግባባት ላይ መድረሱ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በህግ የተሰጠውን ሀላፊነት መሠረት በማድረግ አጀንዳዎችን ከምክክር ሂደቱ ተሳታፊዎች፣ ከተለያዩ ጥናቶች፣ ግለሰቦች ወይም ተቋማት ከሚሰጧቸው የአጀንዳ ሀሳቦች በማሰባሰብ የመለየት፣ የመቅረጽ እንዲሁም ቅደም ተከተል በማስያዝ ምክክር እንዲደረግባቸው ያደርጋል፡፡

ምክክር የሚደረግባቸውን አጀንዳዎች የመቅረጽና ይፋ የማድረግ ብቸኛ ስልጣን ያለው የኮሚሽኑ ም/ቤት ነው፡፡ በመሆኑም በተለያዩ መንገዶች የሚሰበሰቡት የአጀንዳ ሀሳቦች እንጂ ያለቀላቸው አጀንዳዎች አይደሉም፡፡

የአጀንዳ ሀሳቦች ከነማንና እንዴት ይሰባሰባሉ?

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የምክክር አጀንዳ ሀሳቦች በዋናነት ከሶስት ምንጮች ይሰባሰባሉ፡፡

ከወረዳና ከክልል/ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከፌደራለልና ከዲያስፖራ ደረጃዎች በኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታ ስነ ዘዴ መሠረት ተወክለው የአጀንዳ ሀሳቦችን ለመስጠት የተወከሉ ተሳታፊዎች በሚታደሙባቸው በክልል ወይም በከተማ አስተዳደር እንዲሁም በፌደራልና በዲያስፖራ ደረጃ በሚዘጋጁ መድረኮች እንዲሰባሰቡ ይደረጋሉ፡፡

ከሕዝባዊ መደረኮች

እነዚህ ተወካዮች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ ተቋማትንና ማህበራትን ወክለው ወይም ባላቸው ተቀባይነትና ተጽእኖ ፈጣሪነት በኮሚሽኑ እንዲሳተፉ የተመረጡ እንደመሆናቸው መጠን በተለያዩ ደረጃዎች የአጀንዳ ሀሳቦችን የማመንጨት ሂደቱ ይከናወናል፡፡ ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ለተሳታፊዎች አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ የውይይቱም ዋና ትኩረት በሀገራዊ ምክክሩና ለዚህም በሚያስፈልጉ አጀንዳዎች ይዘት ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡ የዚህም ዋነኛ ግብ ምክክር ሊደረግባቸው የሚችሉ አጀንዳዎች ባህሪያትና ይዘት ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ኮሚሽኑ በየአከባቢው ያሉ ችግሮችን ሁሉ የመፍታት ስልጣን የሌለው ከመሆኑም ባሻገር ሁሉም ችግሮች በምክክር የማይፈቱ መሆናቸው ላይ ግንዛቤ እንዲያዝበት ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም መሆኑ በሀገራዊ ምክክር ሊታዩ የሚገባቸውን ሀሳቦች በሌሎች መንገዶች ሊፈቱ ከሚገባቸው ጉዳዮች ለይቶ ለማየትና በውስን ጊዜ ጠቃሚ የአጀንዳ ሀሳቦችን ለማሰባሰብ እድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡

በዚህ መልኩ የአጀንዳ ሀሳቦችን ከሁሉም መድረኮች የማሰባሰቡ ሂደት ብቁ በሆኑ አመቻቾችና አወያዮች እንዲመራ ይደረጋል፡፡ ለዚህም ኮሚሽኑ ገለልተኛ የሆኑና ብቃት ያላቸውን አመቻቾችና አወያዮች የመለየት ስራ እያከናወነ ነው፡፡

በየደረጃው የሚካሄዱ የአጀንዳ መሰባሰቢያ መድረኮች በጋራና በተናጥል የሚካሄዱ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የጋራ የሆኑ የአጀንዳ ሀሳቦችን ለመለየት በተናጥል በቡድን በቡድን በመሰባሰብ ተጓዳኝ ውይይቶች ይደረጋሉ፡፡ ለምሳሌ በክልል ከተለያዩ ወረዳዎችና በክልል ደረጃ የሴት ማህበረሰብ ክፍልን የወከሉ ተሳታፊዎች በጋራ በመሰባሰብ በተለይም ከሴቶች አኳያ ሀገራዊ ናቸው የሚሏቸውን የአጀንዳ ሀሳቦች ለይተው እንዲያወጡ ይደረጋል፡፡ አርሶና አርብቶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን እና ሌሎችም በተመሳሳይ ተጓዳኝ ምክክሮችን ያካሂዳሉ፡፡ በዚህ መልኩ በየቡድኑ የተካሄዱ የአጀንዳ ሀሳቦች ማሰባሰቢያ ተጓዳኝ መድረኮች ወደ ጠቅላላ ክልላዊ ጉባኤ መጥተው እጅግ መሠረታዊና ሀገራዊ የሆኑ የአጀንዳ ሀሳቦች እንዲለዩ ይደረጋል፡፡ እነዚህም በአግባቡ ተሰንደውና ለኮሚሽኑ ም/ቤት ቀርበው በቀጣይ አጀንዳዎችን ለመቅረጽ ለሚከናወነው ተግባር መነሻ ሆነውና ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ጥቅም ላይ አንዲወሉ ይደረጋል፡፡

ከሕዝባዊ መደረኮች 02
 
ሀገራዊና እጅግ መሠረታዊ ናቸው የሚሏቸውን የአጀንዳ ሀሳቦች ግለሰቦች፣ቡድኖችና ተቋማት በቀጥታ ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡበት የአሰራር ስርአትም ተዘርግቷል፡፡ ይህም መሆኑ በሂደቱ በተለያዩ ምክንያቶች አልተወከልንም የሚሉ አካላትን ለማካተትና ለማሳተፍ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ በተለይም ተቋማትና ቡድኖች በራሳቸው መንገድ ጥናቶችን በማድረግ የአጀንዳ ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ በማድረግ የአጀንዳ ሀሳቦችን የማሰባሰብ ስራውን ይበልጥ አካታችና አሳተፊ በማድረግ ሳይዳሰሱ የሚቀሩ ጉዳዮች እንዳይኖሩ ከፍ ያለ ሚና ይኖረዋል፡፡

አጀንዳ ቀረጻ

ከላይ በተገለጹት መንገዶች የተሰባሰቡትን የአጀንዳ ሀሳቦች በፈርጅ በፈርጁ የማጠናቀርና ቅርጽ የማስያዝ ተግባር ቀጣዩ ሂደት ነው፡፡ ከተሰባሰቡት የአጀንዳ ሀሳቦች መካከል እጅግ መሠረታዊና ሀገራዊ፣ የልዩነት መንስኤዎችን የሚዳስሱ እንዲሁም ጥልቀትና አግባብነታቸውን በመመዘን አጀንዳ የመቅረጽ ሂደቱ ይከናወናል፡፡ በዚህ መንገድ የተቀረጹት አጀንዳዎች ለሕዝብና ለባለድርሻ አካላት ይፋ ተደርገውና ቅደም ተከተል ተሰጥቷቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ መድረኮች ምክክር እንዲደረግባቸውና መግባባት ላይ እንዲደረስባቸው ይደረጋል፡፡

አጀንዳ ቀረጻ