የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ተባባሪዎች

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ራሱ የሚመራውና የሚከታተለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተሳታፊ ልየታ ሥራ ላይ እገዛን ያደርጉልኛል ብሎ ያመነባቸውን የሚከተሉትን ሰባት ተባባሪ አካላት ለይቷል፡፡

 

– የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ምክር ቤት

– የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

– የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

– የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የእድሮች ማህበራት ጥምረት

– የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋሟት ጉባኤ

– የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች

– የወረዳ (ልዩ ወረዳ) አስተዳደር ተወካዮች

 

እነዚህ አካላት የሂደቱን ግልጸኝነት፣አሳታፊነት፣ አካታችነት እና ተዓማኒነት በመታዘብና በማረጋገጥ ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ፡፡ ለሂደቱም መሳካት እያንዳንዱ ተባባሪ አካል በየወረዳው (ልዩ ወረዳው) የሚገኙ መዋቅሮቹን በመጠቀም ካሉት አባላት (ባለሙያዎች) አንድ ሰው ለየወረዳው ይወክላል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ኮሚሽኑ ለዚህ ሥራ ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ የተለያዩ መመሪያዎችንና የሥልጠና ማንዋሎችን ያዘጋጀ ሲሆን የኮሚሽኑ አባላትና ሰራተኞችም ሂደቱን በቅርብ የሚከታተሉ ይሆናል፡፡