የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 348 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሲያካሂድ የነበረውን የተሳታፊዎች ልየታ ስራ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

mergedimages

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በሀረር፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ክላሰተር ሲያካሂድ የነበረውን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት ማጠናቀቁን በማስመልከት የመዝጊያ መርሀ-ግብር በሻሸመኔ ከተማ አካሂዷል፡፡ በዚህ የመዝጊያ መርሀ-ግብር የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን ዓርዓያ፣ ም/ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ እና ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌጡ ( ዶ/ር) ተገኝተዋል:: የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን ዓርዓያ ባደረጉት ንግግር […]

ከምስራቅ ጉጂ ዞን 11 ወረዳዎች የመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ወኪሎቻቸውን መረጡ::

436300216 423265033728265 3717769399222700432 n

በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ያለው የሻሸመኔ ክላስተር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡ በሻሸመኔ ክላስተር ስር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እየተከናወነ በሚገኘው የተወካዮች ምርጫ ሂደት ዛሬ ሚያዚያ 08/2016 ዓ.ም ከምስራቅ ጉጂ ዞን 11 ወረዳዎች የመጡ ህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮቻቸውን መርጠዋል፡፡ በምስራቅ ጉጂ ዞን ውስጥ የሚገኙ 11 ወረዳዎች፡- ዋደራ፣ ዳማ፣ አናሶራ፣ አረዳ […]

ጃፓን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለምትሰራው ስራ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ገለፁ፡፡

436384331 422547580466677 7408357033304379797 n

የጃፓን መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 12 ተሸከርካሪዎችን በዛሬው ዕለት አስረክቧል፡፡ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ልገሳው የጃፓን መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት ያለውን ድጋፍ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ቅልጥፍና ልገሳው ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም አክለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለምትሰራው ስራ የጃፓን መንግሥት ወደፊትም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል […]

The People and the Government of Japan, in collaboration with the UNDP, demonstrated its continued commitment to fostering sustainable peace in Ethiopia by donating 12 field vehicles to the Ethiopian National Dialogue Commission.

436356376 422507937137308 1055310495834207559 n

Today, on April 15, 2024, the People and the Government of Japan, in collaboration with the UNDP, demonstrated its continued commitment to fostering sustainable peace in Ethiopia by donating 12 field vehicles to the Ethiopian National Dialogue Commission. During the event, Shibata Hironori, the Japanese Ambassador to Ethiopia, emphasized Japan’s dedication to supporting Ethiopia’s national […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሻሸመኔ ክላስተር በሚገኙ ስድስት ዞኖች በወረዳና ከተማ አስተዳደር ደረጃ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት አስጀመረ፡፡

436235046 421359473918821 6427262530941620310 n

በመክፈቻ መርሀግብሩ ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) እና አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ተገኝተዋል። ኮሚሽነር አምባዬ በመክፈቻ ንግግራቸው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊዎች የተወከሉበትን የማኅበረሰብ ክፍል አውድ በተመለከተ በቂ ግንዛቤ ያዳበሩ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን ገልፀዋል። ገለልተኛ ተቋማትና አጋሮችን በማሳተፍ ሥራዎችን ማከናወኑንና ወደፊትም እንደሚያከናውንም አብራርተዋል፡፡ ኮሚሽነር ዮናስ በበኩላቸው ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና […]

ፅናት ለኢትዮጵያ ማህበር ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ (ዲሲ ግብረ ሀይል) ጋር በመቀናጀት “በምክክር ሀገር ትዳን” የሚል ዘመቻ በማስተባበር ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

image (1)

ማህበሩ “በምክክር ትዳን ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ትላንት መጋቢት 26/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡ የፅናት ኢትዮጵያ ማህበር አባል አቶ ፋሲል አጥሌ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካላት የሚስተዋሉ አለመግባባቶች ወደ ግጭት እየተሸጋገረ የሀገር አንድነት እና ህልውና እየፈተነ ቆይቷል፣ ዛሬም በመፈተን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ግጭቱና አለመግባባቱ ወደ ብሔራዊ ቀውስ ከመግባቱ በፊት ሩቅ ሆኖ ከመብሰልሰል “በምክክር ትዳን […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች

tibebu tadesse

የተሳታፊዎች ልየታን በተመለከተ ኮሚሽኑ በመላው ኢትዮጵያ ከ1ሺ 300 በላይ ወረዳዎችና በክልል የሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊዎችን ለመለየት አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለው አፈጻጸም ከ850 በላይ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በአጀንዳ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ እስካሁን በነበረው ተሳታፊዎችን የመለየት ሂደት ከ130ሺ በላይ ዜጎች ተሳትፈዋል፡፡ እነዚህ 130ሺ የህብረተሰብ ክፍሎች በአጠቃላይ 14ሺ በላይ […]

ንግድ ለሰላም፡ “የንግዱ ማህበረሰብ ተሳትፎ በሚመጣው የሀገራዊ ምክክር” በሚል ርእስ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

435972025 416612701060165 657927

ኢንሼቲቭ አፍሪካ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከንግዱ ማህበረሰብ የተወጣጡ ተወካዮች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር የሚያስችል የውይይት መድረክ አካሄዷል፡፡ በውይይቱም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶና ኮሚሽነር ብሌን ገ/መድህን ተገኝተው በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ እስከ ትግበራው ድረስ የተከናወኑ ስራዎች በዋናነት የተሳታፊዎች ለየታ ከአማራና […]

ጃፓን ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ የምታደረገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር አረጋገጡ፡፡

endc japan

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ በውይይቱም በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አሁናዊ ተግባራት በተመለከተ በዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጻ እና ማብራርያ ተደርጎላቸዋል፡፡ አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገላፃ እና ማብራሪያ ምስጋና አቅርበው በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የምክክር ሂደት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ባለሙሉ ተስፋ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ሀገራቸው ጃፓንም […]