የኮሚሽኑ ልዑክ ከተለያዩ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል
ነሀሴ 1/2017 ዓ.ም
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኮሚሽኑ ልዑካን ቡድን በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል፡፡
ቡድኑ ትላንት ሀምሌ 30/2017 ዓ.ም ከታቦን ቤኪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ተወያይቷል፡፡
ቡድኑ በዚሁ ዕለት በደቡብ አፍሪካ በእውነትና እርቅ ኮሚሽን ስራዎች ላይ ተመራማሪ የሆኑ ምሁራንንም አግኝቶ ተነጋግሯል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ ሀገሪቱ ያቀናው የኮሚሽኑ ልዑክ በደቡብ አፍሪካ ቆይታው ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር አጀንዳዎችን አሰባስቦ የሚመለስ ይሆናል፡፡





