የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀመረ

2i0a0041
የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀመረ
ግንቦት 22/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የምክክር ምዕራፍ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ በይፋ ጀምሯል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ(ፕሮፌሰር) የጋራ እሴቶቻችንን የሚጎዱ የሀሳብ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ጦር አማዘው ብዙ ዋጋ አስከፍለውናል ብለዋል።
ዛሬ የተጀመረው የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የምክክር መድረክ 14ኛ አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች በምክክሩ ሂደት ላይ ያልተሳተፉ አካላትና የማህበረሰብ ክፍሎች የሂደቱ አካል እንዲሆኑ መንግሥትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ዋና ኮሚሽነሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዛሬ የተጀመረው የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የምክክር መድረክ እንደ ሀገር የገጠሙንን ችግሮች ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑንም ገልፀዋል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የተለያዩ የፌደራል ባለድርሻ አካላትን የወከሉ ከ800 በላይ የተቋማት እና ማህበራት ወኪሎች የሂደቱ ተሳታፊዎች ይሆናሉ፡፡