“ሀገራዊ ችግሮችን ከሥረ መሠረታቸው ለመፍታት ሴቶች ያላቸው ክህሎት የላቀ ነው!” ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “በሀገራዊ ምክክሩ የሴቶች ተሳትፎና ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ፤ ሀገራዊ ምክክር በአካታችነት መርህ የሚመራ መኾኑን ማረጋገጥ ለዘላቂ ሰላም ጠቃሚ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ግጭቶችና ሥር የሰደዱ ችግሮችን ለመፍታት ከሀገራዊ ምክክር ሌላ መፍትሔ እንደሌለም ገልጸዋል። ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የሚሳተፉት መብታቸው ስለኾነ […]