ኮሚሽኑ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አወያዮችን መረጣ በማጠናቀቅ ላይ ነው
ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የአወያይነት ሚናን የሚጫወቱ ግለሰቦችን መረጣ እያጠናቀቀ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ የእነዚህን አወያዮች ምርጫ ሲያካሂድ የተለያዩ መስፈርቶችን መጠቀሙ ነው የተገለፀው።
ኮሚሽኑ መስፈርቱን አሟልተው ለተለዩ አወያዮች ከሰኞ ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅት እንዳጠናቀቀም ለማወቅ ተችሏል።
ስልጠናውም አወያዮች በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ወቅት የሚኖሩ ውይይቶች የምክክር ዓውድን ባገናዘ፣ በብቃት፣ በታማኝነት እና በገለልተኝነት እንዲመሩ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ይጠበቃል፡፡


