የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ከምስራቅ ጉጂ ዞን 11 ወረዳዎች የመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ወኪሎቻቸውን መረጡ::

436300216 423265033728265 3717769399222700432 n

በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ያለው የሻሸመኔ ክላስተር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

በሻሸመኔ ክላስተር ስር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እየተከናወነ በሚገኘው የተወካዮች ምርጫ ሂደት ዛሬ ሚያዚያ 08/2016 ዓ.ም ከምስራቅ ጉጂ ዞን 11 ወረዳዎች የመጡ ህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮቻቸውን መርጠዋል፡፡

በምስራቅ ጉጂ ዞን ውስጥ የሚገኙ 11 ወረዳዎች፡- ዋደራ፣ ዳማ፣ አናሶራ፣ አረዳ ጂላ፣ አዶላ፣ ሀሮወላቡ፣ ሰባቦሩ፣ አጋዋዩ፣ ኦዳሻኪሶ፣ ኡራጋ እና ግርጃ የተባሉ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ከአስራ አንዱ ወረዳዎች 880 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሻሸመኔ ክላስተር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በነገው ዕለትም በተመሳሳይ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

436300216 423265033728265 3717769399222700432 n