የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ይጀመራል- ኮሚሽኑ

img 20260612 194810 431

“ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ይጀመራል” ኮሚሽኑ

ሰኔ 5/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚጀምርበትን ቀን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ አብስሯል።

የብስራቱን መግለጫ በንባብ ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር)፤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ሳምንታት  በአዲስ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከናወን  ገልጸዋል። 

ኮሚሽኑ ግልጽና አሳታፊ የምክክር ምዕራፎችን ሲዪከናውን መቆየቱን በማስታወስ፤ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ  1234 ኸረዳዎች መሳተፋቸውን ይህም የኢትዮጵያን 93 በመቶ አካባቢዎች የሸፈነ መሆኑን አመላክተዋል።

ቀጣዩ እና ዋነኛው የኮሚሽኑ ተግባር፤ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በሰለጠነ መንገድ መመካከር እና ዘላቂ መግባባት ላይ መድረስ መሆኑን  ዋና ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

የምክክር ጉባኤው ውጤት  ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮቻችን ተፈትተው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እንዲሁም ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት ጽኑ መሰረት የሚጣልበት ስለመሆኑም አስረድተዋል።

በጉባኤው  ከ12 ክልሎች፣ ከአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፌደራል ባለ ድርሻ አካላት የተወከሉ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ የተናገሩት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ሀገር አቀፍ ጉባኤው ከሚጀመርበት አንድ ሳምንት ቀደም ብለው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተጠቃልለው ይገባሉ ብለዋል።

እስካሁን በምክክር ሂደቱ ያልተሳተፉ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ ኮሚሽኑም ይህን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ጥሪ ጨምረው አብራርተዋል።

በምክክር ጉባኤው ከአራት ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።