የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች መዳረሻቸው የት ነው?

cropped favicon.png
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው የአጀንዳ ልየታ የምክክር ምዕራፍ መድረክ አጀንዳዎች ከባለድርሻ አካላት መሰብሰባቸው ይታወቃል፡፡ ታዲያ እነዚህ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች በምን መልኩ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ይቀርባሉ?
• በምክክር ምዕራፉ ከአዲስ አበባ ከተማ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ከፌዴራል፣ ከክልሎች እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሆነው ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡ በተመሳሳይ በሌሎች አማራጮች ከዜጎች የሚመጡ አጀንዳዎችም ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡
• ለኮሚሽኑ ምክር ቤት የሚቀርቡትን አጀንዳዎች የኮሚሽኑ ምክር ቤት በሚያዘጋጀው አሰራር ስርዓት መሰረት በየፈርጁ ለይቶ ያዘጋጃቸዋል፡፡
• የተዘጋጁት አጀንዳዎች ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አመቺ በሆነ መልኩ ኮሚሽኑ በመቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይቀርጻቸዋል፡፡
• ኮሚሽኑ የቀረጻቸውን የአጀንዳ ስብስቦች ለህዝብ በማሳወቅ እና በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ተሳታፊ የሚሆኑ ባለድርሻ አካላትን በመጋበዝ የመጨረሻ የሆነውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ያካሂዳል፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!

favicon