በትግራይ ክልል የሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር የሰነቃቸው ተስፋዎች
12/5/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ከሚገኙ የክልል ባለድርሻ አካላት፣ የፌዴራል ባለድርሻ አካላት እና በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ማሰባሰቡ ይታወቃል፡፡ በቅርቡም በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት ለመጀመር እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
የትግራይ ክልል ለዓመታት በግጭት ዓውድ ውስጥ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ለትግራይ ባለድርሻ አካላት ምን ዓይነት በጎ ውጤቶችን እንደሚያስገኝ መተንተኑ ኮሚሽኑ በክልሉ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ውጤታማ ከማድረጉም በላይ የባለድርሻ አካላትን የነቃ ድጋፍ እና ተሳትፎ እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡
ከዚህ አኳያ የሚከተሉት ሀሳቦች ሂደቱ ለትግራይ ባለድርሻ አካላት ብሎም ለመላው ኢትዮጵያዊያን የሚያበረክተውን በጎ አስተዋፅኦ ያብራራሉ፡፡
1. የፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድምፆችን ማሰማት
በዚህ ሂደት እንዲሳተፉ ግብዣ እየቀረበላቸው ያሉ አካላት የተለያዩ አቋሞች እንደሚኖሯቸው ቢጠበቅም በሂደቱ ላይ መሳተፋቸው በፖለቲካዊ፣
https://web.facebook.com/EthioNDC





