የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በስዊዲን የሚገኘው የኮሚሽነሮች ልዑክ በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ጋር ተወያየ፡፡

stockholm engagement

በስዊዲን የሚገኘው የኮሚሽነሮች ልዑክ በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ጋር ተወያየ፡፡
መስከረም 22/2018 ዓ.ም(ስቶክሆልም)
በስዊዲን የሚገኘው የኮሚሽሮች ልዑካን ቡድን በስዊድን ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ጋር ትላንት መስከረም 21/2017 ዓ.ም ተወያይቷል፡፡
ልዑኩ ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ፣ ከዓለም አቀፉ የዲሞክራሲ እና የምርጫ አጋዥ ድርጅት (IDEA) እንዲሁም ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (SIDA) ተወካዮች ጋር ገንቢ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡
በውይይቶቹ ላይ የተገኙት ኮሚሽነሮች ኮሚሽኑ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡ በገለፃቸውም ኮሚሽኑ የአካታችነት፣ የግልፅኝነት እና የገለልተኝነት መርሆዎችን በመተግበር ምክክር እያካሄደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዚሁ ገለፃ ኮሚሽኑ በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ማብራሪያ ቀርቧል፡፡
በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት አካላት በበኩላቸው ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እያከናወነች ያለችውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት እንደሚያደንቁ ገልፀው ሂደቱን ለመደገፍ ያላቸውን ፉላጎት እና የሂደቱን ስኬት ለማየት ያላቸውን ጉጉት ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኖርዲክ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚሰባስብበትና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን የሚለይበት መድረክ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 24/2018 ዓ.ም በስቶክሆልም ከተማ ያካሂዳል፡፡