የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በምክክሩ የሴቶች ተሳትፎ ከ45 በመቶ በላይ እንዲሆን እየተሰራ ነው- ኮሚሽኑ

q1
በምክክሩ የሴቶች ተሳትፎ ከ45 በመቶ በላይ እንዲሆን እየተሰራ ነው- ኮሚሽኑ
ሰኔ 23/2017 ዓ.ም
ኮሚሽኑ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ከ45 በመቶ በላይ ሴቶች እንዲወከሉ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ይህንንም ለማሳካት ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር እየሠራ ነው ተብሏል።
በምክክር ሂደት ሴቶችን ማሳተፍ የተሟሉ ማህበረሰባዊ መፍትሔዎችን ለማፍለቅ እንደሚያስችል ተገልጿል።
ሴቶች የማህበረሰቡ ግማሽ በመሆናቸው በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳይ ላይ አስተዋጿቸው ከፍተኛ እንደሆነም ተመላክቷል።
የኮሚሽኑ የሥርዐተ ጾታና አካታችነት ዘርፍ አስተባባሪ ወይዘሮ አበባየሁ ደሳለኝ በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን መፍጠር የሚቻለው ሴቶችን በማካተት እንደሆነም አስረድተዋል።
ይህ መረጃ የተገለፀው ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሠራተኞች ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ሴቶች በምክክሩ ሂደት ስላላቸው ተሳትፎ በተወያዩበት መድረክ ነው።
እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ምክክር ሴቶች በወረዳ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ በፌደራል ባለድርሻ አካላት፣ በታዛቢነት፣ በሞደሬተርነት፣ በአሠልጣኝነትና በበጎ ፈቃደኝነት እየተሳተፉ እንደሚገኙ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።