የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

“ምክክሩን አሳታፊና አካታች የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ኮሚሽኑ

screenshot 20260508 170319 facebook

“ምክክሩን አሳታፊና አካታች የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ኮሚሽኑ

ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ ቆይተው ወደ ሰላም ከተመለሱ አካላት ጋር ያደረገውን የሦስት ቀናት ውይይት አጠናቋል፡፡

የውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ኮሚሽኑ አካታችነትንና አሳታፊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም በትጥቅ ትግል ቆይተው ወደ ሰላም የተመለሱ ወገኖች አጀንዳ እንዲሰጡና በምክክሩ በንቃት እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሰሞኑን ለሶስት ቀናት በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና የሰላምን መንገድ መርጠው ከተመለሱ ወገኖች ጋር የተደረገው ውይይት የዚህ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።

በቅርቡ እነዚህ ወገኖች አጀንዳዎቻቸውን ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ ባለፉት ሦስት ቀናት በነበረው ውይይት ከኮሚሽኑ ጋር ይበልጥ ተቀበራርበው የምክክሩን ሂደት በሚያግዙበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል ብለዋል።

መሰል መድረኮች በሌሎች ክልሎች ከሚገኙ የቀድሞ ታጣቂዎች ጋርም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ኮሚሽኑ አካታችነትና አሳታፊነትን ለማስፈን እስከ ሀገራዊ ጉባኤው ድረስ የጀመራቸውን ጥረቶች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፅንኦት ሰጥተዋል።

በየትኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ታጥቀው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት አሁንም ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ወደሚረጋገጥበት የምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።