የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሲዳማ ክልል ከሚገኙ የወጣቶች፣ የሴቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፤ የሀይማኖት መሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች እንዲሁም የዞን፣ የወረዳ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

endc sidama

ይህ መድረክ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ረቂቅ የተሳታፊዎች መለያና አጀንዳ ማሰባሰብ የአሰራር ሥርዓት (methodology) ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓቶቸንና አስተያየቶችን ለማግኘት ከሚያዘጋጃቸው የውይይት መድረኮች አንዱ ነው፡፡

በሀዋሳ ከተማ በሚደረገው ውይይት ስለኮሚሽኑ ተግባራትና ኃላፊነቶች፣ስለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ ስለፓርትነርሺፕ አስፈላጊነትና አብሮነት፣ ስለአወያዮችና አመቻቾች መረጃዎችን በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በተጨማሪም ስለምክክር ጽንሰ ሃሳብና ለምክክሩ ስኬታማነት የሚያስፈልጉ ነገሮች ላይም ገለጻ ቀርቧል፡፡ እነዚህን መሠረት በማድረግ ተሳታፊዎች በቡድን ሆነው በመወያያ ነጥቦች ላይ ተወያይተው ግብዓቶችን ሰጥተዋል፡፡

 

sidama 3

sidama 2