የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማካሪ ኮሚቴ በ13 አበይት ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ምክረ-ሀሳቦችን ያካተተ ሰነድ ዛሬ በኮሚሽኑ ፅ/ቤት አቅርቦ ውይይት አድርጓል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የአማካሪ ኮሚቴው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያቀርባቸው ምክረ-ሀሳቦች የኮሚሽኑን ስራዎች ለማሻሻል ትልቅ ሚናን እንደሚጫወቱ ገልፀዋል፡፡
የኮሚሽኑ የአማካሪ ኮሚቴ በሙያቸው፣ በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በህዝብ ዘንድ ባላቸው ቅቡልነት እንዲሁም ለሀገራቸው ባበረከቱት አስተዋፅኦ አንቱታን ያተረፉ አባላትን በማካተት ግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ.ም ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡