የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተሳታፊዎችን እያስመረጠ ነው፡፡

east shewa

በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ በተካሄደው መድረክ 600 የሚጠጉ የሊበን ጩቃላ፣ ሉሜ፣ ሞጆ፣ ፈንታሌ፣ ቦራ ፣ ቦሰት እና አደአ ወረዳዎች ተሳታፊዎችን በማካተት እየተከናወነ ይውላል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡  ተሳታፊዎቹ ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦችን ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡