የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን  የተሳታፊ ልየታ እያደረገ ይገኛል፡፡

metekel

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በግልገል በለስ ከተማ መምህራን ኮሌጅ አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሃ-ግብር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡

በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው የተወካዮች መረጣ ከግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር፣ ዳንጉር ወረዳ፣ ፓዌ ወረዳ እና ማንዱራ ወረዳ በአጠቃላይ 400 ተሳታፊዎች ተካፋይ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡

በመርሃ ግብሩ መሰረት በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ለተሳታፊዎች ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ሰለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች በኮሚሽኑ ባለሙያ ገለፃ በመደረግ ላይ ነው፡፡ ከሰዓት በኋላ በሚቀጥለው መርሃ ግብርም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦችን ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡