የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ ሲያስመርጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
የክልሉ የተወካዮች መረጣ 12 ዞኖችን በማካተት ሲከናወን የቆየ ሲሆን 9,300 የሚሆኑ ተሳተፊዎችን የሂደቱ አካል አድርጓል፡፡
በዚሁ ክንውን ተሳታፊዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወክሏቸውን ተወካዮቻቸውን ከመምረጣቸው ባሻገር በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡ በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸውም ገንቢ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡