የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን የተሳታፊ ልየታ እያደረገ ይገኛል፡፡

401235477 333141006074002 8548509446813908312 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በጀሙ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው የመጀመሪያው ዙር መርሃ-ግብር ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡

በዞኑ በአጠቃላይ የ7 ወረዳዎችን እና የ3 ከተማ አስተዳድር የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የሚካሄደው የተወካዮች መረጣ በድምሩ 1000 የሚሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን ያሳትፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሂደቱም ከእያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል አስር አስር ሰዎች የሂደቱ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው የተወካዮች መረጣ ከሻሻ ወረዳ፣ ጎሪጌሻ ወረዳ እና ጀሙ ከተማ የተውጣጡ ተሳታፊዎች የመርሃ-ግብሩ ተካፋይ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡

በመርሃ ግብሩ መሰረት ለተሳታፊዎች ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ሰለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች በኮሚሽኑ ባለሙያ ገለፃ በመደረግ ላይ ነው፡፡ በመቀጠልም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦችን ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡