#እናስታውስዎ!
#ህዳር 20/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት በ9 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ አጀንዳን በህዝባዊ ውይይቶች ሰብስቧል፡፡ በቅርቡም በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት አጀንዳን ይሰበስባል፡፡
በዚህ ሂደት ባለድርሻ አካላት ተብለው የተለዩት እና ኮሚሽኑ በአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ውስጥ እያሳተፋቸው የሚገኙት አካላት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
- በየወረዳው ከሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተመረጡ ተወካዮች
- የሃይማኖት ተቋማት
- የመምህራን ማህበር
- የሲቪል ማህበራት
- ክልላዊና ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች
- የአሰሪዎች ማህበራት
- የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን
- የአካል ጉዳተኞች ማህበራት
- የሙያ ማህበራት
- የክልል መንግስት (አስፈጻሚ አካላት)
- የክልል ዳኞች
- የክልል ምክር ቤት
- ታዋቂ ሰዎች
- የሚዲያ ተቋማት (ጋዜጠኞች) ማህበር
- የቀድሞ ሰራዊት ማህበራት
- የንግድ ማህበራት ምክር ቤት
- የሴቶችና የወጣቶች ማህበራት
- የዩኒቨርሲቲ መምህራን
- የመንግስት ሰራተኞች
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!