ኢንሼቲቭ አፍሪካ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከንግዱ ማህበረሰብ የተወጣጡ ተወካዮች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር የሚያስችል የውይይት መድረክ አካሄዷል፡፡
በውይይቱም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶና ኮሚሽነር ብሌን ገ/መድህን ተገኝተው በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ እስከ ትግበራው ድረስ የተከናወኑ ስራዎች በዋናነት የተሳታፊዎች ለየታ ከአማራና ከትግራይ ክልሎች በስተቀር መጠናቀቁና በአጀንዳ አሰባሰብ ላይ የአሰራር ስርአቱ ምን እንደሚመስል አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶችን ጨምሮ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተመሳሳይ የንግዱ ማህበረሰብን እንደ አንድ ማህበራዊ መሰረት በመቁጠር በአጀንዳ አሰባሰቡ ሂደት ላይ የሚወከልበትም አሰራር መፈጠሩ ተመላክቷል፡፡
በመድረኩም የንግዱ ማህበረሰብ ተሳትፎን ለማጠናከር በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡