ሀገራዊ አጀንዳ ምን አይነት ቅርፅ ሊኖረው ይችላል?
ጥር 26/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 መቋቋሙ የሚታወስ ነው፡፡
በዚሁ አዋጅ መግቢያ ላይ በሀገራችን ኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የፓለቲካ እና የሀሳብ መሪዎች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች መኖራቸው ተጠቅሶ ይህም ለኮሚሽኑ መመስረት እንደምክንያት ተቀምጧል፡፡
👉እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ሊባሉ የሚችሉ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?
ይህንን ጉዳይ ለመረዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ መገንዘብና መሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን ማየት ይጠይቃል፡፡
በእርግጥ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየን የአጀንዳ አይነቶችን በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ መገደብና መወሰን ሂደቱን ለትችት ከመዳረጉም በላይ ተዓማኒነቱን ሊያሳጣው እንደሚችል ዕሙን ነው፡፡
በመሆኑም ኮሚሽኑ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ያሻል ብለው ያመኑባቸውን የአጀንዳ ሀሳቦች በህዝባዊ ውይይቶች እንዲያነሱ ሲያበረታታ ቆይቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችሉ ወሳኝና እጅግ መሰረታዊ የሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮቻችንን ወደ ጠረጴዛ አምጥቶ ምክክር ማድረግ ትርፋማ ያደርገናል፡፡
ለመሆኑ መግባባት የሚጠይቁን ‘’እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች’’ ምን ዓይነት ዋና ዋና መገለጫ እና ቅርፅ እንዲኖራቸው ይጠበቃል?
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጉዳዮች ይህንን ጉዳይ በምሳሌነት ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡
👉የሀገረ መንግሥት ሕልውን እና ቅቡልነትን የሚፈታተኑ ጉዳዮች፤
👉እንደ ሀገር በጋራ ስንኖር በየጊዜው አለመግባባቶችን እያስከተሉ ሀገራዊ አንድነታችንን የሚሸረሽሩ ጉዳዮች፤
👉በአፋጣኝ እልባትን የሚሹ ወቅታዊ ሀገራዊ ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!