የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል የተባባሪ አካላት ስልጠና መስጠት ጀምሯል

401433585 335736559147780 8972404782134505446 n

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ሲሰጥ የነበረውን የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከስድስት ዞኖች የተውጣጡ ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነውበታል፡፡ በስልጠናው ላይ ተባባሪ አካላቱ ባደረጓቸው የቡድን ውይይቶች ላይ የክልሉን ዓውድ መሰረት አድርገው ከየማህበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎችን ስለሚለዩባቸው መንገዶች ውይይቶች አድርገዋል፡፡ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት […]

ኮሚሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን የተሳታፊ ልየታ እያደረገ ይገኛል፡፡

401235477 333141006074002 8548509446813908312 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በጀሙ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው የመጀመሪያው ዙር መርሃ-ግብር ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡ በዞኑ በአጠቃላይ የ7 ወረዳዎችን እና የ3 ከተማ አስተዳድር የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ […]

ኮሚሽኑ አዲስ በተቋቋመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ጥቅምት 22 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ በሆሳዕና ከተማ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

401016875 332634969457939 816547885170058521 n

በክልሉ ከሚገኙ 55 የወረዳ አስተዳደሮች እና 27 ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 574 ሰልጣኝ ተባባሪ አካላት እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ እንዲያደርጉ አቅማቸውን ለማጎልበት ነው፡፡ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ የሚሰጠው ይህ ስልጠና ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ነው፡፡ በዚሁ ቆይታ ሰልጣኝ ተባባሪ አካላቱ ስለ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ […]

ኮሚሽኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል

398672628 328559586532144 1388509867297744658 n

ኮሚሽኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ በሆሳዕና ከተማ ለሶስት ቀናት የተለያዩ ስነ-ዘዴዎችን በመጠቀም ሲሰጥ የነበረው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በተሳታፊ ልየታ ሂደት እና አተገባበር ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ ከ7 ዞኖች እና 3 ልዩ ወረዳዎች ተውጣጥተው ስልጠናውን የወሰዱት ተባባሪ አካላት የተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ተዓማኒና ገለልተኛ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን  የተሳታፊ ልየታ እያደረገ ይገኛል፡፡

metekel

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በግልገል በለስ ከተማ መምህራን ኮሌጅ አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሃ-ግብር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡ በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው የተወካዮች መረጣ ከግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር፣ ዳንጉር ወረዳ፣ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን የመጀመሪያ ውይይት በመቀሌ ከተማ አካሄደ፡፡

tigray

በኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የተመራውና ሌሎች 4 ኮሚሽነሮችን ያካተተው የኮሚሽኑ ልዑካን ቡድን ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ መቀሌ ጉዞውን አድርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡ ኮሚሽኑን ወክሎ የተጓዘው ቡድን ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር ተገናኝቶ የተወያየ ሲሆን በቀጣይ በክልሉ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ለመተግበር የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አሰራር ኮሚሽኑ […]

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙት አባገዳዎች እና ሀደሲንቄዎች ጋር ተወያይቷል

oromia

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ  ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አዘጋጀ፡፡ በመድረኩ ላይ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች የተገኙ ሲሆን በክልሉ በሚከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና እና ተሳትፎ በሰፊው ተብራርቶ ውይይት በመደረግ ላይ ነው፡፡ በዝግጅቱ ላይ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ሌሎች የኮሚሽኑ አባላት ተገኝተዋል፡፡ […]

ኮሚሽኑ ከወጣቶች ማህበራት እና በወጣቶች ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ውይይቶችን አካሄደ፡፡

for youth

መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሚሽኑ አዘጋጅነት በካፒታል ሆቴል የተደረገው ውይይት ከ7 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ላይ የሚሰሩ ማህበራትን እና ድርጅቶችን ተሳታፊ አድርጓል፡፡ የውይይት መድረኩ ሁለት ዓላማዎችን አንግቦ የተነሳ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣቶች በማህበራቱ እና በድርጅቶቹ በኩል ስለ ሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ግንዛቤን እንዲጨብጡ ማድረግ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ወጣቶች በምክክር ሂደቱ ላይ የጎላ ሚና እንዲኖራቸው ሀሳቦችን በማመንጨት ወደ […]

ኮሚሽኑ በአፋር ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወከሉትን ተወካዮች እንዲመረጡ የማድግ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

afar

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአፋር ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከህዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሂደቱም በተለያዩ ምዕራፎች የሚከናወን ሲሆን ዛሬ በተጀመረው የመጀመሪያው ዙር መርሀ-ግብር ላይ ከዞን አንድ ሰመራ እና ሎጊያ ወረዳዎች በሂደቱ ላይ ተሳታፊዎች በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ የክልሉ ርዕሰ-መዲና በሆነችው ሰመራ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ […]

ኮሚሽኑ በአፋር ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

afar

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአፋር ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ከዛሬ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በክልሉ ከሚገኙ 48 ወረዳዎች ለተውጣጡ 380 ሰልጣኝ ተባባሪ አካላት በሰመራ ከተማ እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ እንዲያደርጉ አቅማቸውን ለማጎልበት […]