የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአጀንዳ አሰባሰብ አሰራር ስርዓቱ የሚያግዙ ግብዓቶችን ከባለድርሻ አካላት ሰበሰበ፡፡
ኮሚሽኑ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያካሂደው አጀንዳ የማሰብሰብ ተግባር ያዘጋጀውን ረቂቅ የአሰራር ስርዓት በሚመለከተታቸው ባለድርሻ አካላት አስተችቶ ግብዓቶችን ሰብስቧል፡፡ በአዲስ አበባ ሀይሌ ግራንድ ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ መርሐ-ግብር ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ከ250 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲሁም ከመንግስት እና ከሌሎች የሚመለከታቸው […]
“የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡” ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብና የሀገራዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች የግብአት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይት መድረኩ ከተለያዩ ማኅበራት፣ ተቋማትና የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወከሉ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ለውይይቱ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሂደቱ ላይ በንቃት […]
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ!
መልካም የዒድ አልፈጥር በዓል ይሁንላችሁ! የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
ኮሚሽኑ በሰሜን ሸዋ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ አስመርጧል፡፡
በአዳማ ከተማ በተካሄደው በዚህ መርሐ-ግብር በዞኑ የሚገኙ ከ1,500 በላይ ተሳታፊዎች ወረዳዎቻቸውን እና የማህበረሰብ ክፍሎቻቸውን በመወከል እንዲሳተፉ አስችሏል፡፡ በሂደቱ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች በባለሙያ ገላፃ ካደረገላቸው በኋላ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ አድርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ዛሬ ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡
በፊልቱ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው መርሐ-ግብር ከደቃ ሱፍቱ፣ ቀርሳ ዱላ እና ፊልቱ ወረዳዎች የተውጣጡ ተሰብሳቢዎችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡ በሂደቱ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች በባለሙያ ገላፃ ያደረገ ሲሆን ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች በመምረጥ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሊበን ዞን የተወካዮች መረጣ ቅዳሜ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ እና ጎፋ ዞኖች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ አስመረጠ፡፡
በአርባ ምንጭ እና ሳውላ ከተሞች በትይዩ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የጋሞ እና ጎፋ ዞኖች የተወካዮች መረጣ ከየወረዳው የተወከሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን በማካተት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የጋሞ ዞን የተወካዮች መረጣ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን 1,800 የሚሆኑ ተሳታፊዎች 20 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በመወከል ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ መርሐ-ግብሩም የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል […]
ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ በማስመረጥ ላይ ይገኛል፡፡
በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ 1,300 የሚሆኑ የሁሉም ክፍለ ከተሞች ተሳታፊዎችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡ በሂደቱም ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በመቀጠልም ውይይቶች ይደረጉና ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ […]
ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን አስመረጠ፡፡
በሞያሌ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ተቋም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከሙባረክ፣ ሞያሌ፣ ቀዳዱሞ እና ሁደት ወረዳዎች የተውጣጡ 400 የሚሆኑ ተሰብሳቢዎች ተሳትፈዋል፡፡ በሂደቱም ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ መሰረት ተሳታፊዎች ለአጀንዳ […]
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሳምንታዊ አበይት ክንውኖች
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሳምንታዊ አበይት ክንውኖች
ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን የተለያዩ የህበብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተወካዮችን መረጣ አከናወነ፡፡
ተወካዮችን የማስመረጡ ሂደት በክልሉ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት የምዕራብ አርሲን 14 ወረዳዎች ያሳተፈ መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡ በሂደቱ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በመቀጠልም ውይይት ተደርጎ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ […]