ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን እያደራጁ ነው
#ኦሮሚያ ክልል ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን እያደራጁ ነው በኦሮሚያ ክልል የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ከትላንት ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም ጀምረው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት እያደራጁ ይገኛሉ። ባለድርሻ አካላቱ ያደራጁትን አጀንዳ ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡ 25 ተወካዮችን መርጠው በአደራ ያስረክባሉ። እነዚህ የሚመረጡ 25 ወኪሎች በነገው ዕለት የክልሉን አጀንዳ በዋና መድረክ አቅርበው በማፀደቅ ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ ይሆናል። በኦሮሚያ […]
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት አባላት በምክክሩ እየተሳተፉ ነው፡፡
ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት አባላት ተናገሩ፡፡ በቅርቡ ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረመው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ የምክክሩን አስፈላጊነት አፅኦት ሰጥቶ፣ የኦሮሞ ህዝብም ምክክሩ ሰላም ያመጣል የሚል እምነት እንዳለው […]
የኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በይፋ ተጀመረ
ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ሁለተኛው ምዕራፍ የሆነው የባለድርሻ አካላት ምክክር ዛሬ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ጨፌ ኦሮሚያ መሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል፡፡ በዚህ መድረክ 320 የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ ከ1ሺ 700 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አካላት፣ የተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች […]
በኦሮሚያ ክልል የወረዳ የማኅበረሰብ ክፍሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር እየተካሄደ ነው።
8/4/2017 በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ትናንት ጠዋት በይፋ በተከፈተው የምክክር መድረክ ከ356 የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ7000 በላይ የማኅበረሰብ ክፍል ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መርሐግብር ጀምረዋል። በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የማኅበረሰብ ክፍሎች ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ዕድሮች፣ መምህራን፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ራሳቸውን የማገልጹበት መተዳደሪያ ያላቸው፣ ተፈናቃዮች፣ በባህላቸውና በሙያቸው ምክንያት የተገለሉ፣ ነጋዴዎች እና የማኅበረሰብ መሪዎች ናቸው። ተሳታፊዎቹ በ4 […]
የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀመረ።
ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የሚያከናውነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ዛሬ ጠዋት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) በኢትዮጵያ ያሉ የአለመግባባት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት መመካከር አስፈላጊ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ እጅግ መሠረታዊ የአለመግባባት መንስኤዎችን በአጀንዳ መልክ በማሰባሰብ ስኬታማ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም […]
#ኦሮሚያ ክልል
#ኦሮሚያ ክልል #ህዳር 30/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍን ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ መርሃ-ግብሩ ከታህሳስ 7 እስከ 15 ቀናት 2017 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ ይካሄዳል፡፡ በሂደቱም፦ 👉7020 የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች 👉356 ወረዳዎች 👉1700 የክልል ባለድርሻ አካላት 👉48 ሞደሬተሮች 👉356 የክልሉ ተባባሪ አካላት 👉150 በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች ይሳተፋሉ፡፡ Komishiniin […]
የአካል ጉዳተኞች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ በንቃት የመሳተፋቸው አስፈላጊነት
የአካል ጉዳተኞች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ በንቃት የመሳተፋቸው አስፈላጊነት ህዳር 24/2017 ዓ.ም የሀሳብ ልዩነቶች የሰላም እጦትን፣ ግጭትን እና መፈናቀልን ሲያስከትሉ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚጎዱ ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው፡፡ በተለይም የዚህ ጉዳት ዋነኛ ሰለባዎች የአካል ጉዳተኞች ናቸው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአካል ጉዳተኞች የሚገኙ ሲሆን እነሱም በሀገራችን የስነ-ህዝብ ምጣኔ ከአንድ አስረኛ በላይ […]
ኮሚሽኑ በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እያሳተፋቸው የሚገኙት ባለድርሻ አካላት
#እናስታውስዎ! #ህዳር 20/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት በ9 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ አጀንዳን በህዝባዊ ውይይቶች ሰብስቧል፡፡ በቅርቡም በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት አጀንዳን ይሰበስባል፡፡ በዚህ ሂደት ባለድርሻ […]
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ ለምን አስፈለገ?
ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲካሄድ ሁለት መነሻ ምክንያቶች አሉ። የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የሀሳብ መሪዎች እንዲሁም የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነት እና አለመግባባት መኖሩ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል የፖለቲካ ባህል ለማዳበር እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ምቹ መደላድል መፍጠር […]
#መልካም ቀንመልካም ሳምንት
#መልካም ቀንመልካም ሳምንት ህዳር 16/2017 ዓ.ም #ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!