የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጅማ ክላስተር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት አስጀመረ።

jima 1

ኮሚሽኑ ዛሬ ከጅማ ክላስተር ከአሥር ወረዳዎች ተመርጠው ከመጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል፤ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት አስጀምሯል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ተሳታፊዎች፣ ተባባሪ አካላት፣ የጅማ ማኅበረሰብ አባላትና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሂደቱን ለማገዝ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በቅድመ ዝግጅት፣ በዝግጅትና በትግበራ ምዕራፍ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዚህ ሳምንት ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት

tibebu t

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች የውክልና ሂደት በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በ12 ዞኖች ከሚገኙ 97 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች 9,300 የሚሆኑ ዜጎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በቀጣይ በሚካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ ከ1500 የማያንሱ ተወካዮች በክልል ደረጃ በሚካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የክልሉን ነዋሪ ወክለው ይሳተፋሉ፡፡ ———————- በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዚህ ሳምንት ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት

weekly

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የተመራ የኮሚሽኑ ልዑክ ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡ ኮሚሽኑ በሌሎች ክልሎች ያከናወናቸውን ስራዎች በአማራ ክልልም ማስቀጠል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ያደረገው፡፡ በአማራ ክልል በኩል የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ኃላፊዎች በውይይቱ የተሰታፉ ሲሆን  ርዕሰ መስተዳደሩ የምክክር ኮሚሽኑ በቀጣይ በክልሉ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ውጤታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ […]

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲያካሂድ የቆየውን የተወካዮች መረጣ አጠናቀቀ፡፡

south et

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ ሲያስመርጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የክልሉ የተወካዮች መረጣ 12 ዞኖችን በማካተት ሲከናወን የቆየ ሲሆን 9,300 የሚሆኑ ተሳተፊዎችን የሂደቱ አካል አድርጓል፡፡ በዚሁ ክንውን ተሳታፊዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወክሏቸውን ተወካዮቻቸውን ከመምረጣቸው ባሻገር በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ግንዛቤ […]

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ በማስመረጥ ላይ ይገኛል፡፡

kore zone

በኬሌ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር በዞኑ ከሚገኙ 2 ወረዳዎች እና 1 የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 300 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ተወካዮች ከአንድ ተጠባባቂ ጋር እንዲመርጡ ይደረጋል፡:

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ አስመረጠ፡፡

south omo

በቱርሚ ከተማ የተካሄደው ይህ መርሐ-ግብር ከስድስት ወረዳዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 700 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ተከናውኗል፡፡ በሂደቱ ለተሳታፊዎቹ በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ እንዲሁም በሂደቱ በተወካይ ተሳትፎ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡርጂ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ይገኛል፡፡

burji zone

በሶያማ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከአንድ ወረዳ እና አንድ የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 200 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ በሂደቱ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች በባለሙያ ገላፃ የተደረገላቸው ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአጀንዳ አሰባሰብ አሰራር ስርዓቱ የሚያግዙ ግብዓቶችን ከባለድርሻ አካላት ሰበሰበ፡፡

addis ababa 1.

ኮሚሽኑ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያካሂደው አጀንዳ የማሰብሰብ ተግባር ያዘጋጀውን ረቂቅ የአሰራር ስርዓት በሚመለከተታቸው ባለድርሻ አካላት አስተችቶ ግብዓቶችን ሰብስቧል፡፡ በአዲስ አበባ ሀይሌ ግራንድ ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ መርሐ-ግብር ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ከ250 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲሁም ከመንግስት እና ከሌሎች የሚመለከታቸው […]

“የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡” ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ

addis ababa 2

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብና የሀገራዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች የግብአት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይት መድረኩ ከተለያዩ ማኅበራት፣ ተቋማትና የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወከሉ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ለውይይቱ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሂደቱ ላይ በንቃት […]