የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በአዳማ ከተማ የውይይት መድረኮችን አካሂዷል

347136482 1433881280853606 3101540898748078607 n

ታህሳስ 22-23 ቀናት 2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የዞኖችና ወረዳዎች ኃላፊዎች ጋር በአዳማ ከተማ የውይይት መድረኮችን አካሂዷል፡፡ በሁለቱ ቀናት የውይይት መድረኮች ተሳታፊዎች ኮሚሽኑ ባዛጋጃቸው የአሰራር ስርዓቶች ላይ አስተያቶችን የሰጡ ሲሆን በቡድን ውይይቶችን በማካሄድ በርካታ ግብዓቶችን ሰጥተዋል፡፡

ሰብዓዊ መብትን የሚመለከቱ የመወያያ አጀንዳዎች ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ቀረቡ

endc human rights

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት፣ የሰብዓዊ መብትና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ለመወያያ ይሆናሉ ያላቸውን አጀንዳዎች፣ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቀረበ፡፡ ኅብረቱ ማክሰኞ ታኅሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው የምክክር መድረክ፣  አጀንዳዎቹን ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተወካዮች ሲያቀርብ የኅብረቱ ኃላፊዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ለአገራዊ ምክክሩ የሚሆኑ የሰብዓዊ መብት አጀንዳዎችን በአራት በመክፈል፣  ከአሥራ አንዱ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች አንደኛው […]

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በጎዴ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የተባባሪ አካላት ስልጠና አጠኗቋል

endc gode trining

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ጎዴ ማዕከል ለተባባሪ አካላት ሲሰጥ የነበረውን ሀለተኛውን ዙር ስልጠና ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቀቀ፡፡ በጎዴ ከተማ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከአምስት ዞኖች የተውጣጡ ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነውበታል፡፡ በስልጠናው ላይ ተባባሪ አካላቱ ባደረጓቸው የቡድን ውይይቶች ላይ የክልሉን ዓውድ መሰረት አድርገው ከየማህበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎችን ስለሚለዩባቸው መንገዶች ውይይቶች አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩልም […]

ኮሚሽኑ በአፋር ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወከሉትን ተወካዮች እንዲመረጡ የማድረግ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአፋር ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከህዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሂደቱም በተለያዩ ምዕራፎች የሚከናወን ሲሆን ዛሬ በተጀመረው የመጀመሪያው ዙር መርሀ-ግብር ላይ ከዞን አንድ ሰመራ እና ሎጊያ ወረዳዎች በሂደቱ ላይ ተሳታፊዎች በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ የክልሉ ርዕሰ-መዲና በሆነችው ሰመራ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትውውቅና የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ አካሄደ፡፡

endc bahirdar

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ውጤታማ እንዲሆን የአማራ ክልል መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል” – ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የግጭት መነሻ የሚሆኑ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህላችን ሊጎለብት ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ገለፁ።   የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ከአማራ ክልል መንግሥት የካቢኔ አባላት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከወጣቶች ተወካዮች ጋር ትውውቅ እያደረጉ ነው።   በትውውቅ መድረኩ የአማራ […]

የኢትዮጵ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የትውውቅና የምክክር መድረክ በጂጂጋ ከተማ አካሄደ፡፡

የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች መካከል በአምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር፣ በዶ/ር ዮናስ አዳዬ እንዲሁም በዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ የተመራው ቡድን ወደ ሶማሌ ክልል ዋና መቀመጫ ጂጂጋ ከተማ አቅንቶ ከክልሉ መስተዳድር እና የካቢኔ አባላት ጋር የትውውቅ እና ውይይት መድረክ አከናውኗል፡፡ መድረኩም  የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር በአምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር ስለ ጉብኝታቸው ዕቅድ አጠር ያለ ማብራሪያ ካቀረቡ በኃላ ስለ […]

ኮሚሽኑ በሲዳማ ክልል ከሚገኙ የወጣቶች፣ የሴቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፤ የሀይማኖት መሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች እንዲሁም የዞን፣ የወረዳ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

endc sidama

ይህ መድረክ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ረቂቅ የተሳታፊዎች መለያና አጀንዳ ማሰባሰብ የአሰራር ሥርዓት (methodology) ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓቶቸንና አስተያየቶችን ለማግኘት ከሚያዘጋጃቸው የውይይት መድረኮች አንዱ ነው፡፡ በሀዋሳ ከተማ በሚደረገው ውይይት ስለኮሚሽኑ ተግባራትና ኃላፊነቶች፣ስለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ ስለፓርትነርሺፕ አስፈላጊነትና አብሮነት፣ ስለአወያዮችና አመቻቾች መረጃዎችን በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በተጨማሪም ስለምክክር ጽንሰ ሃሳብና ለምክክሩ ስኬታማነት የሚያስፈልጉ ነገሮች ላይም ገለጻ ቀርቧል፡፡ እነዚህን መሠረት […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል (1/3/2015)።

endc civil societies

በስምምነቱ መሰረት ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የምክክር ሂደቱን ለማገዝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚኖራቸውን አዎንታዊ ሚና የሚያጎላ ነው ተብሎ ይታመናል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ሰነዱ ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት “የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራው ውስብስብ ቢሆንም ዛሬ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር […]

ኮሚሽኑ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል

323452724 2315268528655706 8912462945688164677 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ባለው ውይይት ላይ የተለያዩ ጉዳዮች አንስቶ ገለፃዎችን አድርጓል፡፡ የኮሚሽኑ አባላት የሀገራዊ ምክክርን ፅንሰ ሀሳብ በውይይቱ ላይ ያብራሩ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም ሀገራዊ ምክክሮችን ለማድረግ የተከናወኑ የዝግጅት ስራዎችን አቅርበዋል፡፡ ከቀረቡት የዝግጅት ስራዎች ውስጥ ተሳታፊዎችን ለመለየት የተደረጉ ዝግጅቶች ዋናውን ቦታ የሚይዙ ሲሆን በቀጣይ ሊሰሩ […]