ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ አስመረጠ፡፡
በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ በተካሄደው መርሐ-ግብር ከ12 ወረዳዎች የተውጣጡ ተሰብሳቢዎች ተሳትፈውበታል፡፡ በሂደቱም ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ገለጻውን ተከትሎ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ ተደርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ በማስመረጥ ላይ ይገኛል፡፡
በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ለአንድ ቀን እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡ በመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ገለጻውን ተከትሎ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት […]
ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ነው፡፡
በዲላ እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች በትይዩ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የጌዴኦ ዞን እና የወላይታ ዞን የተወካዮች መረጣ ከየወረዳው የተወከሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን በማካተት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዲላ ከተማ የጌዴኦ ባህል አዳራሽ እየተከናወነ የሚገኘው የጌዴኦ ዞን የተወካዮች መረጣ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን 1,300 የሚሆኑ ተሳታፊዎች 13 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በመወከል ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በወላይታ ሶዶ ከተማ […]
ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡
በዋርዴር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአጠቃላይ ከ 7 ወረዳዎች የተወከሉ 700 ተሳታፊዎችን ያሳትፋል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ገለታውን ተከትሎ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ […]
ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች በተባባሪ አካላት ስልጠና ላይ ሳይካተቱ ለቆዩ ወረዳዎችን ተባባሪ አካላት ስልጠና ሰጠ፡፡
በ8 ዞኖች ውስጥ ከሚገኙ 55 ወረዳዎች የተወከሉ 185 የሚሆኑ ተባባሪ አካላት የተሳተፉበት ይህ ስልጠና ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ሲሰጥ ቆይቶ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ስልጠናውን የወሰዱ ተባባሪ አካላት ከኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ከአባገዳዎች፣ ከሀደ ሲንቄዎች ከማህበረሰብ መሪዎች፣ ከክልሉ ሲቪክ ማህበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ መምህራን ማህበር፣ የዕድሮች […]
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሳምንታዊ አበይት ክንውኖች
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሳምንታዊ አበይት ክንውኖች
ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን እያስመረጠ ነው፡፡
ከየካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሺኒሌ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአጠቃላይ 1100 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን ያሳትፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመድረኩ ከአይሻ፣ ሀዳጋላ እና ሺኒሌ ወረዳዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ ተገኝተዋል፡፡ መርሐ-ግብሩ በተመሳሳይ ሁኔታ በቀጣዮቹም ሁለት ቀናት የተቀሩትን የዞኑን ወረዳዎች በማሳተፍ ይቀጥላል፡፡ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር […]
ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ነው፡፡
የዞኑ የተወካዮች መረጣ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተከናወነ ሲሆን ከ10 ወረዳዎች የተውጣጡ 1,200 የሚሆኑ የተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮች ተሳታፊ እየሆኑበት ይገኛል፡፡ በመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል […]
ኮሚሽኑ ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚሁ መድረክ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደቶች ላይ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ግንዛቤን ለመፍጠር ታስቦ በተዘጋጀው መድረክ ከ 250 በላይ የተቋማት ተወካዮች ታድመውበታል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ኮሚሽኑንና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ የተለያዩ ገለፃዎችና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሰረት ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፣ ሀገራዊ ምክክር ለሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ፋይዳ፣ […]
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተሳታፊዎችን እያስመረጠ ነው፡፡
በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ በተካሄደው መድረክ 600 የሚጠጉ የሊበን ጩቃላ፣ ሉሜ፣ ሞጆ፣ ፈንታሌ፣ ቦራ ፣ ቦሰት እና አደአ ወረዳዎች ተሳታፊዎችን በማካተት እየተከናወነ ይውላል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ […]