የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡

somali dolo

በዋርዴር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአጠቃላይ ከ 7 ወረዳዎች የተወከሉ 700 ተሳታፊዎችን ያሳትፋል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ገለታውን ተከትሎ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ […]

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች በተባባሪ አካላት ስልጠና ላይ ሳይካተቱ ለቆዩ  ወረዳዎችን ተባባሪ አካላት  ስልጠና ሰጠ፡፡

oromia participants

በ8 ዞኖች ውስጥ ከሚገኙ 55 ወረዳዎች የተወከሉ 185 የሚሆኑ ተባባሪ አካላት የተሳተፉበት ይህ ስልጠና ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ሲሰጥ ቆይቶ  የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ስልጠናውን የወሰዱ ተባባሪ አካላት ከኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ከአባገዳዎች፣ ከሀደ ሲንቄዎች ከማህበረሰብ መሪዎች፣ ከክልሉ ሲቪክ ማህበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣  መምህራን ማህበር፣  የዕድሮች […]

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን እያስመረጠ ነው፡፡

siti zone

ከየካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሺኒሌ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአጠቃላይ 1100 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን ያሳትፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመድረኩ ከአይሻ፣ ሀዳጋላ እና ሺኒሌ ወረዳዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ ተገኝተዋል፡፡ መርሐ-ግብሩ በተመሳሳይ ሁኔታ በቀጣዮቹም ሁለት ቀናት የተቀሩትን የዞኑን ወረዳዎች በማሳተፍ ይቀጥላል፡፡ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር […]

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ነው፡፡

arsi zone

የዞኑ የተወካዮች መረጣ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተከናወነ ሲሆን ከ10 ወረዳዎች የተውጣጡ 1,200 የሚሆኑ የተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮች ተሳታፊ እየሆኑበት ይገኛል፡፡ በመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡  ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል […]

ኮሚሽኑ ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር  ውይይት አደረገ፡፡

private colleges

በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚሁ መድረክ  የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደቶች ላይ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ግንዛቤን ለመፍጠር ታስቦ በተዘጋጀው መድረክ ከ 250 በላይ የተቋማት ተወካዮች ታድመውበታል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ኮሚሽኑንና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ የተለያዩ ገለፃዎችና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሰረት ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፣ ሀገራዊ ምክክር ለሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ፋይዳ፣ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተሳታፊዎችን እያስመረጠ ነው፡፡

east shewa

በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ በተካሄደው መድረክ 600 የሚጠጉ የሊበን ጩቃላ፣ ሉሜ፣ ሞጆ፣ ፈንታሌ፣ ቦራ ፣ ቦሰት እና አደአ ወረዳዎች ተሳታፊዎችን በማካተት እየተከናወነ ይውላል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡  ተሳታፊዎቹ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ  ሚና ከነበራቸው ባለሙያ ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ፡፡

tunisia

በኮሚሽኑ ፅ/ቤት በመገኘት ልምዳቸውን ያጋሩት ዶክተር አህመድ ድሪስ በ2013 በቱኒዚያ የተደረገውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በመጥቀስ ለውይይት ጋባዥ የሆኑ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡ በመድረኩ የኮሚሽኑ አባላት እና ባለሙያዎች ተገኝው ሀሳቦች እና ጥያቄዎችን በማንሳት ገንቢ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረውና በኮሚሽኑ አስተባባሪነት በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ ዛሬም ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ 01

ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረውና በኮሚሽኑ አስተባባሪነት በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ ዛሬም ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጥሎ ውሏል፡፡ በዛሬው መርሃ-ግብር በጅግጅጋ ከተማ በሶማሌ ክልል ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አዳራሽ ውስጥ የፋፈን ዞን የተወካዮች መረጣ በመከናወን ላይ ሲሆን በሂደቱም የሃሮራይስ ወረዳ፣ የቀብሪበያህ ከተማ አስተዳደር፣ የቀብሪበያህ ወረዳ እና የጎልጃኖ ወረዳዎች ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌላ ከኩል በጎዴ ከተማ […]

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 01

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በጅግጅጋ እና ጎዴ ከተሞች በትይዩ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የፋፈን ዞን እና የሸበሌ ዞን የተወካዮች መረጣ ከየወረዳው የተወከሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን በማካተት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የፋፈን ዞን የተወካዮች መረጣ ለሶስት ቀናት የሚቆይ […]