የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ተሳታፊዎች ልየታን በሠላምና በተሳካ አኳኋን አጠናቀቀ፡፡

356430804 256813380373432 4767745042192657120 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲለዩ አድርጓል፡፡ ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተደረገው የተሳታፊዎች ልየታ መርሃ ግብር በከተማ መስተዳድሩ ከሚገኙ ወረዳዎች ከእያንዳንዳቸው የተውጣጡ 9 የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ሰዎችን መርጠው በሂደቱም በቁጥር 4500 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በዚሁ ክንውን […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

365471930 279285424792894 4377453634882040428 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ውይይት አድርጓል፡፡ በኮሚሽኑ አዘጋጅነት የተደረገው የዚህ ውይይት ዓላማ ኮሚሽኑ በጋራ ምክር ቤቱ አጋዥነት በሰራቸው ስራዎች ላይ ገለፃ ለመስጠት እና በቀጣይም በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ውይይቶችን ለማድረግ ነው፡፡ ኮሚሽኑ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ሲያስመርጥ የሂደቱን ግለፀኝነትና […]

ኮሚሽኑ የሐረሪ ክልል የተሳታፊዎች ልየታን በተሳካ ሁኔታ አከናወነ፡፡

354459126 251858394202264 1236656366855401079 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሐረሪ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲለዩ አድርጓል፡፡ በሐረር ከተማ ከሰኔ 5 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገው የተሳታፊዎች ልየታ መርሃ ግብር በክልሉ ከሚገኙ 9 ወረዳዎች የተውጣጡ 9 የማህበረሰብ ክፍሎች እያንዳንዳቸው 50 ሰዎችን መርጠው በሂደቱም ከ 4,000 በላይ ተሳታፊዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡ በዚህም መሰረት በክልሉ በተደረገው የተሳታፊዎች […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ተፈራረሙ

367469692 619872980270745 6285249553532174069 n

በሀገራችን እያታዩ ያሉ ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ በሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ላይ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተካታችነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ተፈራረሙ፡፡ የፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና የአካል ጉዳተኛ ማህበር ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ስልጠናን ሰጠ፡፡

357017049 261080386613398 2362755868503674080 n

በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት እና አተገባባር ላይ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ያለመው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው የሚገኙ ተሳታፊዎችን በመለየቱ ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ ስለሚያደርጉበት መንገድ ግንዛቤን አስጨብጧል፡፡ ስልጠናው ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ የተሰጠ ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ 22 ወረዳዎችና 5 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 200 ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ ከስልጠናው በተጨማሪም ሰልጣኝ ተባባሪ አካላቱ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠና ሰጠ

380692651 303794372341999 8321647713476058257 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠና ሰጠ፡፡ የሁለት ቀናት ጊዜን የወሰደው ስልጠና በክልሉ ርዕሰ መዲና ጋምቤላ ከተማ ውስጥ ተደርጎ ሰኔ 07 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ከ 14 ወረዳ የተውጣጡ 100 ተባባሪ አካላትን ያሳተፈው ይህ ስልጠና አንድ መሰረታዊ ዓላማን ይዞ የተሰጠ ሲሆን ያም በስልጠናው ላይ የተገኙት ተባባሪ አካላት በየወረዳቸው የሚገኙ ተሳታፊዎችን በመለየቱ […]

ኮሚሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲለዩ አድርጓል፡፡

355277054 255102413877862 3454423605371635448 n

ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም በቦንጋ ከተማ የተጀመረው የተሳታፊዎች ልየታ መርሃ ግብር በቴፒ፣ ማሻ፣ ሚዛን፣ አማን፣ አመያ እና ተርጫ ከተሞች ቀጥሎ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ከ 47 ወረዳዎች ከእያንዳንዳቸው 9 የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ሰዎችን መርጠው በሂደቱም በቁጥር ከ21,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ኮሚሽኑ በክልሉ ባካሄደው የልየታ መርሀ ግብር ተሳታፊዎች በአጀንዳ […]

ኮሚሽኑ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ተሳታፊዎች ጋር ስብሰባን አድርጓል

356417931 259600376761399 3478735563252624723 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡና እያንዳንዳቸውም 9 የማህበረሰብ ክፍሎችን ወክለው ከመጡ 3,600 ተሳታፊዎች ጋር ሐሙስ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ስብሰባን አድርጓል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ አዳራሽ እና በሐዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ የተደረገው ይህ ስብሰባ ለሚቀጥለው የምክክር ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ተግባራት አከናውኗል፡፡ በስብሰባው ላይ ሁለት ክንውኖች የተካሄዱ ሲሆን በጠዋቱ […]

ኮሚሽኑ የሲዳማ ክልል የተሳታፊዎች ልየታን አድርጓል

356247899 259599763428127 4189274986883382439 n

ሰኔ 01 ቀን 2015 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የተጀመረው የሲዳማ ክልል የተሳታፊዎች ልየታ በይርጋለም፣አለታ ወንዶ እና በንሳ ከተሞች ቀጥሎ ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ በክልሉ ከሚገኙ 45 ወረዳዎች ከተውጣጡና በእያንዳንዳቸው ከሚኖሩ ዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ተሳታፊዎች የሂደቱ አካል እንዲሆኑ በማድረግ (በአንድ ወረዳ 450) በአጠቃላይ ከ20,000 በላይ ተሳታፊዎች የሂደቱ ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች በተከናወኑ […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶስት ክልሎችና በአንድ የከተማ መስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠናን ሰጥቷል፡

conclusion 5

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶስት ክልሎችና በአንድ የከተማ መስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠናን ሰጥቷል፡፡ በተሳታፊ ልየታ አተገባበር ላይ የተሰጠው ይህ ስልጠና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ፣ በሲዳማ እና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ለሚገኙ ከየወረዳው ለተውጣጡ የኮሚሽኑ ተባባሪ አካላት ነው፡፡ ስልጠናው በቦንጋ፣ሐዋሳ እና ድሬዳዋ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን የሁለት ቀናት ጊዜን ወስዶ ግንቦት 23 […]