የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትውውቅና የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ አካሄደ፡፡

endc bahirdar

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ውጤታማ እንዲሆን የአማራ ክልል መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል” – ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የግጭት መነሻ የሚሆኑ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህላችን ሊጎለብት ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ገለፁ።   የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ከአማራ ክልል መንግሥት የካቢኔ አባላት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከወጣቶች ተወካዮች ጋር ትውውቅ እያደረጉ ነው።   በትውውቅ መድረኩ የአማራ […]

የኢትዮጵ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የትውውቅና የምክክር መድረክ በጂጂጋ ከተማ አካሄደ፡፡

የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች መካከል በአምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር፣ በዶ/ር ዮናስ አዳዬ እንዲሁም በዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ የተመራው ቡድን ወደ ሶማሌ ክልል ዋና መቀመጫ ጂጂጋ ከተማ አቅንቶ ከክልሉ መስተዳድር እና የካቢኔ አባላት ጋር የትውውቅ እና ውይይት መድረክ አከናውኗል፡፡ መድረኩም  የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር በአምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር ስለ ጉብኝታቸው ዕቅድ አጠር ያለ ማብራሪያ ካቀረቡ በኃላ ስለ […]

ኮሚሽኑ በሲዳማ ክልል ከሚገኙ የወጣቶች፣ የሴቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፤ የሀይማኖት መሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች እንዲሁም የዞን፣ የወረዳ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

endc sidama

ይህ መድረክ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ረቂቅ የተሳታፊዎች መለያና አጀንዳ ማሰባሰብ የአሰራር ሥርዓት (methodology) ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓቶቸንና አስተያየቶችን ለማግኘት ከሚያዘጋጃቸው የውይይት መድረኮች አንዱ ነው፡፡ በሀዋሳ ከተማ በሚደረገው ውይይት ስለኮሚሽኑ ተግባራትና ኃላፊነቶች፣ስለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ ስለፓርትነርሺፕ አስፈላጊነትና አብሮነት፣ ስለአወያዮችና አመቻቾች መረጃዎችን በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በተጨማሪም ስለምክክር ጽንሰ ሃሳብና ለምክክሩ ስኬታማነት የሚያስፈልጉ ነገሮች ላይም ገለጻ ቀርቧል፡፡ እነዚህን መሠረት […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል (1/3/2015)።

endc civil societies

በስምምነቱ መሰረት ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የምክክር ሂደቱን ለማገዝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚኖራቸውን አዎንታዊ ሚና የሚያጎላ ነው ተብሎ ይታመናል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ሰነዱ ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት “የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራው ውስብስብ ቢሆንም ዛሬ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር […]

ኮሚሽኑ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል

323452724 2315268528655706 8912462945688164677 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ባለው ውይይት ላይ የተለያዩ ጉዳዮች አንስቶ ገለፃዎችን አድርጓል፡፡ የኮሚሽኑ አባላት የሀገራዊ ምክክርን ፅንሰ ሀሳብ በውይይቱ ላይ ያብራሩ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም ሀገራዊ ምክክሮችን ለማድረግ የተከናወኑ የዝግጅት ስራዎችን አቅርበዋል፡፡ ከቀረቡት የዝግጅት ስራዎች ውስጥ ተሳታፊዎችን ለመለየት የተደረጉ ዝግጅቶች ዋናውን ቦታ የሚይዙ ሲሆን በቀጣይ ሊሰሩ […]