የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን የመጀመሪያ ውይይት በመቀሌ ከተማ አካሄደ፡፡

tigray

በኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የተመራውና ሌሎች 4 ኮሚሽነሮችን ያካተተው የኮሚሽኑ ልዑካን ቡድን ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ መቀሌ ጉዞውን አድርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡ ኮሚሽኑን ወክሎ የተጓዘው ቡድን ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር ተገናኝቶ የተወያየ ሲሆን በቀጣይ በክልሉ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ለመተግበር የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አሰራር ኮሚሽኑ […]

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙት አባገዳዎች እና ሀደሲንቄዎች ጋር ተወያይቷል

oromia

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ  ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አዘጋጀ፡፡ በመድረኩ ላይ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች የተገኙ ሲሆን በክልሉ በሚከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና እና ተሳትፎ በሰፊው ተብራርቶ ውይይት በመደረግ ላይ ነው፡፡ በዝግጅቱ ላይ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ሌሎች የኮሚሽኑ አባላት ተገኝተዋል፡፡ […]

ኮሚሽኑ ከወጣቶች ማህበራት እና በወጣቶች ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ውይይቶችን አካሄደ፡፡

for youth

መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሚሽኑ አዘጋጅነት በካፒታል ሆቴል የተደረገው ውይይት ከ7 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ላይ የሚሰሩ ማህበራትን እና ድርጅቶችን ተሳታፊ አድርጓል፡፡ የውይይት መድረኩ ሁለት ዓላማዎችን አንግቦ የተነሳ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣቶች በማህበራቱ እና በድርጅቶቹ በኩል ስለ ሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ግንዛቤን እንዲጨብጡ ማድረግ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ወጣቶች በምክክር ሂደቱ ላይ የጎላ ሚና እንዲኖራቸው ሀሳቦችን በማመንጨት ወደ […]

ኮሚሽኑ በአፋር ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወከሉትን ተወካዮች እንዲመረጡ የማድግ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

afar

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአፋር ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከህዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሂደቱም በተለያዩ ምዕራፎች የሚከናወን ሲሆን ዛሬ በተጀመረው የመጀመሪያው ዙር መርሀ-ግብር ላይ ከዞን አንድ ሰመራ እና ሎጊያ ወረዳዎች በሂደቱ ላይ ተሳታፊዎች በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ የክልሉ ርዕሰ-መዲና በሆነችው ሰመራ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ […]

ኮሚሽኑ በአፋር ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

afar

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአፋር ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ከዛሬ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በክልሉ ከሚገኙ 48 ወረዳዎች ለተውጣጡ 380 ሰልጣኝ ተባባሪ አካላት በሰመራ ከተማ እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ እንዲያደርጉ አቅማቸውን ለማጎልበት […]

ኮሚሽኑ የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ተሳታፊዎች ልየታን በሠላምና በተሳካ አኳኋን አጠናቀቀ፡፡

356430804 256813380373432 4767745042192657120 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲለዩ አድርጓል፡፡ ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተደረገው የተሳታፊዎች ልየታ መርሃ ግብር በከተማ መስተዳድሩ ከሚገኙ ወረዳዎች ከእያንዳንዳቸው የተውጣጡ 9 የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ሰዎችን መርጠው በሂደቱም በቁጥር 4500 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በዚሁ ክንውን […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

365471930 279285424792894 4377453634882040428 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ውይይት አድርጓል፡፡ በኮሚሽኑ አዘጋጅነት የተደረገው የዚህ ውይይት ዓላማ ኮሚሽኑ በጋራ ምክር ቤቱ አጋዥነት በሰራቸው ስራዎች ላይ ገለፃ ለመስጠት እና በቀጣይም በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ውይይቶችን ለማድረግ ነው፡፡ ኮሚሽኑ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ሲያስመርጥ የሂደቱን ግለፀኝነትና […]

ኮሚሽኑ የሐረሪ ክልል የተሳታፊዎች ልየታን በተሳካ ሁኔታ አከናወነ፡፡

354459126 251858394202264 1236656366855401079 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሐረሪ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲለዩ አድርጓል፡፡ በሐረር ከተማ ከሰኔ 5 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገው የተሳታፊዎች ልየታ መርሃ ግብር በክልሉ ከሚገኙ 9 ወረዳዎች የተውጣጡ 9 የማህበረሰብ ክፍሎች እያንዳንዳቸው 50 ሰዎችን መርጠው በሂደቱም ከ 4,000 በላይ ተሳታፊዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡ በዚህም መሰረት በክልሉ በተደረገው የተሳታፊዎች […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ተፈራረሙ

367469692 619872980270745 6285249553532174069 n

በሀገራችን እያታዩ ያሉ ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ በሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ላይ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተካታችነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ተፈራረሙ፡፡ የፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና የአካል ጉዳተኛ ማህበር ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር […]

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ስልጠናን ሰጠ፡፡

357017049 261080386613398 2362755868503674080 n

በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት እና አተገባባር ላይ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ያለመው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው የሚገኙ ተሳታፊዎችን በመለየቱ ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ ስለሚያደርጉበት መንገድ ግንዛቤን አስጨብጧል፡፡ ስልጠናው ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ የተሰጠ ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ 22 ወረዳዎችና 5 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 200 ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ ከስልጠናው በተጨማሪም ሰልጣኝ ተባባሪ አካላቱ […]