የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሳምንታዊ አበይት ክንውኖች

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሳምንታዊ አበይት ክንውኖች
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከዛሬ ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከዛሬ ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 10 ወረዳዎችንና 5 የከተማ አስተዳደሮችን የሂደቱ አካል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በሂደቱም ከ1500 በላይ ተሳታፊዎች ወረዳዎቻቸውን […]
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከ60 በላይ ከሚሆኑ የዓለም አቀፍ ተቋማት እና ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በስካይ ላይት ሆቴል ውይይት አድርጓል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ የትብብር እና አጋርነት መድረክ ላይ ኮሚሽኑን ወክለው በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት ኮሚሽነሮች በኮሚሽኑ ስለተከናወኑ ተግባራት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ሁነት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመረዳት ለበለጠ […]
ህትመቶች
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ – አማርኛና እንግሊዝኛ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ – አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ – ትግርኛ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ – ሶማሊኛ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ – አፋርኛ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ – ሲዳምኛ
በአሜሪካ እና ካናዳ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

በአሜሪካ እና ካናዳ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የበይነ-መረብ ስብሰባው ላይ ለመሳተፍ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ፡፡ ይመዝገቡ
ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የዲያስፖራ ማህበር አባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የዲያስፖራ ማህበር አባላት ጋር ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ. ም በሚሊኒየም አዳራሽ ውይይት አድርጓል፡፡ የውይይት መድረኩ በሀገር ውስጥ የሚኖሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባ ንቁ ተሳትፎ እና ሊያደርጉ ስለሚገባው ድጋፍ ግንዛቤን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ መርሐ-ግብሩም በኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፈሰር መስፈን አርያአያ የመክፈቻ ንግግር […]
ኮሚሽኑ በቤኒሻንጉል ክልል የተሳታፊ ልየታ እያደረገ ይገኛል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከጥቅምት 02 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሂደቱም በሁለት ዙር የሚከናወን ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 13 የአሶሳ ዞን ወረዳዎች የሚካተቱበት መርሃ ግብር ይካሄዳል፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላም 14 ወረዳዎች የሚሳተፉበት ሁለተኛው መርሃ ግብር ይካሄዳል፡፡ በክልሉ በአጠቃላይ የ22 ወረዳዎችና የአምስት […]
ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል የተባባሪ አካላት ስልጠና መስጠት ጀምሯል

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ሲሰጥ የነበረውን የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከስድስት ዞኖች የተውጣጡ ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነውበታል፡፡ በስልጠናው ላይ ተባባሪ አካላቱ ባደረጓቸው የቡድን ውይይቶች ላይ የክልሉን ዓውድ መሰረት አድርገው ከየማህበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎችን ስለሚለዩባቸው መንገዶች ውይይቶች አድርገዋል፡፡ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት […]
ኮሚሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን የተሳታፊ ልየታ እያደረገ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በጀሙ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው የመጀመሪያው ዙር መርሃ-ግብር ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡ በዞኑ በአጠቃላይ የ7 ወረዳዎችን እና የ3 ከተማ አስተዳድር የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ […]
ኮሚሽኑ አዲስ በተቋቋመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ጥቅምት 22 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ በሆሳዕና ከተማ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በክልሉ ከሚገኙ 55 የወረዳ አስተዳደሮች እና 27 ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 574 ሰልጣኝ ተባባሪ አካላት እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ እንዲያደርጉ አቅማቸውን ለማጎልበት ነው፡፡ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ የሚሰጠው ይህ ስልጠና ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ነው፡፡ በዚሁ ቆይታ ሰልጣኝ ተባባሪ አካላቱ ስለ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ […]