የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ተወያየ

hay
ኮሚሽኑ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ተወያየ
የካቲት 4/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በምክክሩ ሂደትና ተሳትፎ ዙሪያ ዛሬ የካቲት 4/2017 ዓ.ም ውይይት አድርጓል፡፡
የውይይት መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ኮሚሽኑ ባለፉት ሶስት አመታት ለሰራው ስራና ላስመዘገበው ውጤት የኃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ስኬታማ ውጤቶችን እንዲያስመዘግብ የኃይማኖት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋፅም ዋና ኮሚሽሩ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይ የሚደረገው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን የኃይማኖት ተቋማት የተለመደውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ኮሚሽኑ በሦስት ዓመታት ጉዞ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ክንውኖችና ቀሪ ተግባራትን አስመልክቶ ለተሳታፊ የኃይማኖት አባቶች ገለፃ አድርገዋል፡፡
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የኃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የአሰራር ሥርዓት ምክረ ሀሳብ ቀርቦም ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመድረኩ የተገኙ የኃይማኖት አባቶች በበኩላቸው ኮሚሽኑ በብዙ ፈተናና ውጣ ውረድ ውስጥ ሆኖ በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን እየተወጣ ላለው ታሪካዊ ኃላፊነት አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡
ከቀረበው የአሰራር ስርዓት ምክረ ሀሳብ በመነሳት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የኃይማኖት ተቋማት ሊሳተፉ የሚችሉበትን ሁኔታ በምክር ቤታቸው በኩል ወስነው በአጭር ጊዜ ለኮሚሽኑ እንደሚያሳውቁም ተሳታፊ የሃይማኖት ተቋማት መሪ አባቶች ተናግረዋል፡፡
ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀው ውይይት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ፣ ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር፣ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) እና ኮሚሽነር ዘገዬ አስፋው ተገኝተው በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚሁ መድረክ ተጓዳኝ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለሀገራዊ ምክክሩ ግብዓት እንዲሆኑ ያዘጋጀቻቸውን አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ አስረክባለች፡፡
+6
See insights

Boost a post
All reactions:

You and 27 others

1 comment
1 share
Like

Comment
Send
Share