ኮሚሽኑ ከዪኤንዲፒ ጋር ተባብሮ በውጤት ተኮር ሥራ አመራር፣ በተቋማዊ ባህል፣ በዕቅድ መንደፍና አተገባበር እንዲሁም በውጤት ምዘና ዙሪያ ለተቋሙ የስራ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ለአመራሮቹ እና ባለሙያዎቹ አቅጣጫ የተሰጠበትን ስልጠና የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌጡ (ዶ/ር) እና ኮሚሽነር ብሌን ገ/መድህን ተገኝተው ሰጥተዋል።
ኮሚሽነሮቹ ስራ አመራሮችና ባለሙያዎች በተቀናጀ ሁኔታ በቀሪ አስር ወራት የኮሚሽኑን ስራ እንዴት ማቀላጠፍ እንዳለባቸው በሙያዊና አስተዳደራዊ ማብራሪያ ላይ የተመሰረተ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በቀሪ አስር ወራት ተባብረንና ያለንን አቅም አሟጠን በመጠቀም ስራዎችን መጨረስ አለብን ሲሉ ኮሚሽነሮቹ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም የጀመረው ስልጠናው እስከ ነገ ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል።
የአመራሮችንና የባለሙያዎችን የመፈፀም አቅም ማሳደግ ከስልጠናው የሚጠበቅ መሆኑም ተገልጿል።