በዋርዴር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአጠቃላይ ከ 7 ወረዳዎች የተወከሉ 700 ተሳታፊዎችን ያሳትፋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
ገለታውን ተከትሎ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ተወካዮችን ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡