የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ነው፡፡

arsi zone

የዞኑ የተወካዮች መረጣ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተከናወነ ሲሆን ከ10 ወረዳዎች የተውጣጡ 1,200 የሚሆኑ የተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮች ተሳታፊ እየሆኑበት ይገኛል፡፡

በመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡  ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦች ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡