በክልሉ ከሚገኙ 55 የወረዳ አስተዳደሮች እና 27 ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 574 ሰልጣኝ ተባባሪ አካላት እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ እንዲያደርጉ አቅማቸውን ለማጎልበት ነው፡፡
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ የሚሰጠው ይህ ስልጠና ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ነው፡፡ በዚሁ ቆይታ ሰልጣኝ ተባባሪ አካላቱ ስለ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች፣ ስለ ኮሚሽኑ ዓላማ እና መርሆች እንዲሁም በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ላይ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ግንዛቤን ለመፍጠር የሚያስችል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡