ኮሚሽኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ በሆሳዕና ከተማ ለሶስት ቀናት የተለያዩ ስነ-ዘዴዎችን በመጠቀም ሲሰጥ የነበረው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በተሳታፊ ልየታ ሂደት እና አተገባበር ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡
ከ7 ዞኖች እና 3 ልዩ ወረዳዎች ተውጣጥተው ስልጠናውን የወሰዱት ተባባሪ አካላት የተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ተዓማኒና ገለልተኛ እንዲሆን ለማረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ይጠበቃል::
በመቀጠልም በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት ወደየወረዳዎቻቸው በመሄድ በኮሚሽኑ ከተለዩት የማህበረሰብ
ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ረገድ የሂደቱን ተዓማኒነት በተመለከተ እገዛ ያደርጋሉ፡፡