የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲለዩ አድርጓል፡፡ ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተደረገው የተሳታፊዎች ልየታ መርሃ ግብር በከተማ መስተዳድሩ ከሚገኙ ወረዳዎች ከእያንዳንዳቸው የተውጣጡ 9 የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ሰዎችን መርጠው በሂደቱም በቁጥር 4500 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በዚሁ ክንውን ተሳታፊዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንዲንፀባረቅላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች በቡድን ውይይቶቻቸው አመላክተዋል፡፡