የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠና ሰጠ

380692651 303794372341999 8321647713476058257 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠና ሰጠ፡፡ የሁለት ቀናት ጊዜን የወሰደው ስልጠና በክልሉ ርዕሰ መዲና ጋምቤላ ከተማ ውስጥ ተደርጎ ሰኔ 07 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ከ 14 ወረዳ የተውጣጡ 100 ተባባሪ አካላትን ያሳተፈው ይህ ስልጠና አንድ መሰረታዊ ዓላማን ይዞ የተሰጠ ሲሆን ያም በስልጠናው ላይ የተገኙት ተባባሪ አካላት በየወረዳቸው የሚገኙ ተሳታፊዎችን በመለየቱ ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛን ስለሚያደርጉበት መንገድ ግንዛቤን መፍጠር ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ አባላት ከተባባሪ አካላቱ ጋር በተሳታፊ ልየታ ሂደት፣ አተገባበር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና በግብዓትነት ሊወሰዱ የሚችሉ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ሰልጣኞች ተሳታፊዎችን በማስወከል ሂደት ስለሚኖራችው ገለልተኛ ተሳትፎ በየወረዳቸው በቡድን ሆነው ተወያይተዋል፡፡ በተጨማሪም ኮሚሽኑ በስልጠናው ላይ በተባባሪ አካላቱ ትብብር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን መለየት በሚያስችለው አካሄድ ላይ መክሯል፡፡

በመቀጠልም በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመሄድ በኮሚሽኑ ከተለዩት ዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ረገድ ሂደቱ ተዓማኒ እንዲሆን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡

380694233 303794392341997 182068300482385359 n

380667938 303794132342023 8655126216048245387 n

380166838 303794169008686 3112925842895196149 n

380157353 303794269008676 3336334918486382829 n

380152274 303794119008691 761615886924793895 n