ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የተቀረጹ ስምንት አጀንዳዎች በዝርዝር:-
አጀንዳ ቁጥር 1:- የሀገር ግንባታ
1.1 የማንነት እና የሀገር ባለቤትነት ጉዳዮች
1.2. ታሪክ እና ማንነት
1.3. የጋራ ሀገራዊ ማንነት እና እሴቶች (እሴቶችንም የሚመለከቱ ጉዳዮች)
1.4. ሀገር ግንባታና ብዝሀነት አስተዳደር ጉዳዮች
1.5. የቋንቋ ጉዳዮች
1.6 የባሕል፣ታሪክና ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች
አጀንዳ ቁጥር 2:- የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዐት፣የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት
2.1 የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ
2.1.1 የመንግሥት አደረጃጀት፣አስተዳደር ሥርዐት ዓይነት
2.1.2 የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት
2.1.3 የብሔር ብሔረሰቦች ትርጓሜ
2.1.4 የፌደራል መንግሥት እና የክልል መንግሥታት መሪዎች የሥልጣን ዘመን
2.1.5 የፌደራልና የክልል መንግሥታት ግንኙነት። የሥልጣን ክፍፍል፣የፌደራልና የክልል መንግሥት የፊስካል ፌደራሊዝምና የሀብት ክፍፍል
2.1.6 የክልል አስተዳደር እና ወሰኖች፤ የአዳዲስ ክልሎች አመሠራረት። የክልል አስተዳደራዊ ወሰኖች
2.1.7 የሕግ አውጪው አካል ወይም ፓርላማ አወቃቀርና ሚና
2.1.8 ሕገ መንግሥትን የመተርጎም ሥልጣን
2.1.9 የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሥርዐት
2.2 የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርአት ጉዳዮች
2.2.1 የሀገሪቱ የምርጫ ሥርዐት
2.2.2 የመድብለ ፓርቲ ሥርዐት
2.2.3 የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት
2.2.4 የመንግሥትና የገዢ ፓርቲ ሚና መለያየት
2.2.5 የምርጫ ክልሎች አወቃቀር
2.2.6 የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥት ሀብት አጠቃቀም
አጀንዳ ቁጥር 3:- የፌደራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ)
3.1 የአዲስ አበባ ጉዳይ
3.1.1 የአዲስ አበባ ሕጋዊ አቋም። አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት የአዲስ አበባ ከተማ የበጀት ድርሻ ጉዳይ
3.1.2 የፌደራል ዋና ከተማ ጉዳይ
3.1.3 የአዲስ አበባ ፖሊስና ፍርድ ቤት ጉዳይ
3.1.4 የአዲስ አበባ ወሰንና የቦታዎች ስያሜዎች
3.1.5 የአዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ
3.1.6 የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች፣አካታችነት ጉዳይ
3.2 የድሬዳዋ ጉዳይ
3.2.1 የድሬዳዋ ሕጋዊ አቋም
3.2.2 የድሬዳዋ የወደፊት አስተዳደራዊ ሁኔታ፣የሕዝቦቿ ውክልናና ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጋር ያላት ግንኙነት
3.2.3 የድሬዳዋ በፌደራል መንግሥት ውክልና። ድሬዳዋ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚኖራት ውክልና ጉዳይ
አጀንዳ ቁጥር 4:- የሃይማኖት ጉዳዮች፣ታሪካዊ ቅሬታዎች እና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች
4.1.1 በሴኪውላሪዝምና በሃይማኖት ነጻነት መካከል ጤናማ ሚዛን መጠበቅ
4.1.2 የሃይማኖት ነጻነትና ገደቦቹ
4.1.3 አናሳ የተከታይ ቁጥር ያላቸው ሃይማኖት ተቋማት ጥበቃ
4.1.4 ከባሕል እና ከሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር የሚጋጩ ድርጊቶች ጉዳይ
4.2 ታሪካዊ ቅሬታዎችና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች
4.2.1 ታሪካዊ መገለል እና ልዩ ተጠቃሚነት
4.2.2 የእርቅና እውቅና የመስጠት ሂደት
4.3 በሃይማኖቶች መካከል ስላለው ግንኙነት እና አብሮ መኖርን በተመለከተ
4.3.1 በሃይማኖቶች መካከል ያሉ ውጥረቶችና መፍትሄዎቻቸው
4.3.2 በሃይማኖቶች መካከል የውይይት እና ምክክር ዘዴዎችን ማጠናከር
4.4 ሃይማኖት በሕዝብ ሕይወት እና ማኅበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ያለውን መስተጋብር በተመለከተ
4.4.1 በሕዝብ ተቋማት ውስጥ የሃይማኖት ሚና
4.4.2 የሃይማኖት መድረኮች፣ሚዲያና ሕዝባዊ ውይይቶች
4.4.3 የሃይማኖት ተቋማት የድምጽ አጠቃቀም እና የሕብረተሰብ መብት
አጀንዳ ቁጥር 5:- ተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነትና ሰብአዊ መብቶች
5.1 የሰብአዊ መብቶች
5.1.1 ሕገ መንግሥታዊ እና ሕጋዊ ማእቀፍ ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ
5.1.2 በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች መብቶች
5.1.3 አካል ጉዳት፣ተጋላጭና የተገለሉ ቡድኖች መብቶች
5.1.4 የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በግጭት እና በጸጥታ ሁኔታዎች ውስጥ
5.1.5 ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማዊ ማእቀፎች የማጠናከር ጉዳይ
5.1.6 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ (ዳያስፖራ)። የጥምር ዜግነት መብት እውቅና እና ሌሎች ጉዳዮች
5.2 የሕግ የበላይነት
5.2.1 የህግ የበላይነት (ህጋዊነት)
5.2.2 በሕግ ፊት እኩልነት
5.2.3 ተጠያቂነት
5.2.4 የፍትሕ ተደራሽነት
5.3 የተቋማት ግንባታ
5.3.1 የዲሞክራሲያዊ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ነፃነትና ተደራሽነት
5.3.2 የፍትህ ተቋማት ነፃነትና ተጠያቂነት
5.3.3 የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ነፃነት፣ ገለልተኝነትና አደረጃጀት
5.3.4 የሶስቱ የመንግሥት አካላት ሚዛን፣ ነፃነት እና ተጠያቂነት
5.3.5 የመገናኛ ብዙኃን ተቋማዊ ገለልተኝነት፣ ነፃነት እና ተጠያቂነት
5.3.6 የሲቪል ማኅበራት ነፃነት፣ ሚናና ተጠያቂነት
አጀንዳ ቁጥር 6:- ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች
6.1 ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች
6.1.1 የሴቶች ጉዳይ እና ተያይዘው የቀረቡ ጥያቄዎች
6.1.2 የሀብት አስተዳደር እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል
6.1.3 የመሬት ይዞታና ባለቤትነት
6.1.4. የሕዝብ ቆጠራ ውክልና እና አካታች አስተዳደር
6.1.5 ማኅበራዊ አገልግሎቶች (ጤና፣ ትምህርትና የኑሮ ደረጃ)
6.1.6 የሠራተኛ መብቶች እና ፍትሀዊ የስራ ሁኔታ
6.1.7 ዘላቂ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ
6.1.8 የተፈጥሮ ሀብት መብቶችና ጥቅም መጋራት
6.1.9 አካታች ኢኮኖሚ፣ኢንቨስትመንት እና ምርታማነት
6.1.10 ማኅበራዊ ደኀንነትና የስራ እድል
6.2. የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይ
6.2.1 የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ተሳትፎና እኩልነት ተጠቃሚነትን የማሳደግ ጉዳይ
6.2.2 የግብርና ግብአቶች ወቅታዊና ፍትሐዊ ተደራሽነትን በተመለከተ።
6.2.3 የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 5ና አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 8 ላይ የተጠቀሰውን ‘ዘላን’ የሚለውን ስያሜ ማስተካከል
6.2.4 ነፃ የገበያ እድልና የገበያ ትስስር መፍጠር
6.2.5 የአርሶ አደርና አርብቶ አደር ማኅበረሰቦች የጋራ መልማትና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ
6.2.6 የአርብቶ አደሮች የኑሮ ዘይቤያቸውን ያማከለ የልማት ፖሊሲ
አጀንዳ ቁጥር 7:- ሙስና እና መልካም አስተዳደር
7.1 የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሙስና ጉዳዮች።
7.2 የጸረ-ሙስና ስርአት ግንባታ
7.3 የመልካም አስተዳደር ስርአት ግንባታ
7.4 ፍትሐዊ ፓብሊክ ሰርቪስ
7.4.1ፍትሐዊና አካታች ፓብሊክ ሰርቪስ
7.4.2 በብቃት ላይ የተመሠረተ የሰው ሃብት አመዳደብ እና ቅጥር
አጀንዳ ቁጥር 8:- ሰላም ግንባታ
8.1የግጭት መንስኤዎች እና አፈታት መንገዶች
8.2ግጭቶችንና መሳሪያ ያነሱ አካላትን በሚመለከቱ
8.3 የዘላቂ ሰላም መሠረቶች
8.4 ባሕላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች እውቅና፣ ማጠናከር እና ዘመናዊ ውህደት
8.4.1 ባሕላዊ እውቅና እና ህጋዊ ማእቀፍ
8.4.2 የእርቅና ይቅርታ ጉዳይ
8.4.3 የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነቶች
8.4.4 የሽግግር ፍትሕ
8.5. ሃይማኖት ተቋማት ሚና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን