የኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
ግንቦት 6/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ዘገየ አስፋው ስርዓተ ቀብር የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮችና ባለሙያዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ዛሬ ግንቦት 6/2018 ዓ.ም ተፈፅሟል፡፡
ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከአባታቸው አቶ አስፋው አብዲ ብሩና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሙሉ ዳዲ በ1934 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ እንደተወለዱ የህይወት ታሪክ ማህደራቸው ያመለክታል፡፡
ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከየካቲት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ግንቦት 3/2018 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ኮሚሽነሩ ስራቸውን በአርአያነት፣ በታማኝነት፣ በትጋት እና በሀገር ፍቅር ስሜት ሥራቸውን በከፍተኛ የኃላፊነት ሥሜት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
ኮሚሽነር ዘገየ ባደረባቸው ህመም በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ግንቦት 3/2018 ዓ.ም ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ስርዓተ ቀብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ዛሬ ግንቦት 6/2018 ዓ.ም ተፈፅሟል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለኮሚሽኑ ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡
👉የህይወት ታሪካቸውን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን እንዲያነቡ እንጋብዛለን
https://www.facebook.com/share/p/1BTCyRYEYn/




