የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብ ክፍሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

4d7a9530 min

ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልል የምክክር መድረክ የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች ትናንት ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም በአራት ክላስተር ተከፍለው የቡድን ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ አነስተኛ ቡድኖች በተናጥል አጀንዳቸውን ለይተው ካጠናቀቁ በኋላ አንድ ንዑስ ቡድን በመመስረት አጀንዳዎቻቸውን እያጠናቀሩ ነው። የክልል የህብረተሰብ ወኪሎች ምክክር 80 ንዑስ ቡድኖች ሲኖሩት እያንዳንዱ ክላስተር 20 ንዑስ ቡድን እንዲኖረው ተደርጎ ምክክሩ […]

በኦሮሚያ ክልል የወረዳ የማኅበረሰብ ክፍሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር እየተካሄደ ነው።

oromia 06

8/4/2017 በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ትናንት ጠዋት በይፋ በተከፈተው የምክክር መድረክ ከ356 የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ7000 በላይ የማኅበረሰብ ክፍል ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መርሐግብር ጀምረዋል። በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የማኅበረሰብ ክፍሎች ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ዕድሮች፣ መምህራን፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ራሳቸውን የማገልጹበት መተዳደሪያ ያላቸው፣ ተፈናቃዮች፣ በባህላቸውና በሙያቸው ምክንያት የተገለሉ፣ ነጋዴዎች እና የማኅበረሰብ መሪዎች ናቸው። ተሳታፊዎቹ በ4 […]

የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀመረ።

oromia agenda (3)

ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የሚያከናውነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ዛሬ ጠዋት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) በኢትዮጵያ ያሉ የአለመግባባት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት መመካከር አስፈላጊ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ እጅግ መሠረታዊ የአለመግባባት መንስኤዎችን በአጀንዳ መልክ በማሰባሰብ ስኬታማ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም […]