ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን ለይተው አጠናቀቁ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የምክክር ምዕራፍ ለስድስተኛ ቀን ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ አምስቱ የምክክር ባለድርሻ አካላት ትላንት እና ዛሬ ከሰዓት በፊት በነበረው መርሃ-ግብር የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን በቡድን ሆነው ሲያጠናቅሩና ሲያደራጁ ቆይተዋል፡፡ ባለድርሻ አካላቱ ያጠናቀሯቸውን እና ያደራጇቸውን አጀንዳዎች በቃለ-ጉባኤ በማዘጋጀት ለአጠቃላይ መድረኩ የሚያቀርቡላቸውን ተወካይ ግለሰቦችንም መርጠዋል፡፡ ዛሬ ከሰአት በተካሄደው መርሃ-ግብር […]