የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የሕብረተሰብ ክፍል ወኪሎች አጀንዳዎቻቸውን በቃለ ጉባኤ እያደራጁ ነው፡፡

አዲስ 8

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ 11 የሕብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ከ2000 በላይ ተሳታፊዎች ከግንቦት 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ኹለት ቀናት ከወከሉት የህብረተሰብ ከፍል ይዘው በመጡት አጀንዳ ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮቹ በዚህ ውይይታቸው እጅግ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይተዋል፡፡ በዛሬው የጠዋት መርሃ-ግብር አጀንዳዎቻቸውን በአንድ ቃለ ጉባኤ የሚያደራጁበት ኹነትም በግዮን ሆቴል እየተከናወነ ይገኛል። በተጨማሪም […]

ኮሚሽኑ በምክክሩ ለሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት ገለፃ አደረገ፡፡

አዲስ 7

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ በምክክር ምዕራፍ ላይ ተሳታፊ ለሚሆኑ ባለድርሻ አካላት ገለፃ አድርጓል፡፡ ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የምክክር ምዕራፍን በይፋ ያስጀመረው ኮሚሽኑ ዛሬ ግንቦት 23 ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለተውጣጡ ወኪሎች በአደዋ ሙዚየም አዳራሽ ስለ ምክክር ምዕራፉ ገለፃ እና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በዕለቱ በተዘጋጀው የገለፃ መርሃ-ግብር የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ […]

የሕብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳቸውን ለይተው ለኮሚሽኑ አስረከቡ፡፡

አዲስ 6

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 21 ጀምሮ ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያስተባብር የነበረውን ክንውን ጨርሷል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች በአጀንዳ ሀሳቦች ላይ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት እና ልየታ ዛሬ መቋጫውን አግኝቷል፡፡ የከተማዋን ነዋሪ በተለያዩ ቡድኖች ወክለው የተገኙ ከ2000 በላይ ተወካዮች ከወከላቸው የሕብረተሰብ ክፍል በአደራ በተቀበሏቸው የአጀንዳ ሀሳቦች ላይ ላለፉት ሶስት […]