የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በጋራ አዲስ በተሾሙት የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን የተመራውን የኮሚሽኑን ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች ልዑክ በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አድርገዋል። ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም የተካሄደው ይህ የውይይት መድረክ ሁለቱ ኮሚሽኖች በሚያከናውኗቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሀሳብ ልውውጥ ተደርጎበታል፡