የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ አመራሮችና ባለሙያዎች በቀሪ አስር ወራት የኮሚሽኑን ስራ የሚያቀላጥፉበት አቅጣጫ ተሰጠ፡፡
ኮሚሽኑ ከዪኤንዲፒ ጋር ተባብሮ በውጤት ተኮር ሥራ አመራር፣ በተቋማዊ ባህል፣ በዕቅድ መንደፍና አተገባበር እንዲሁም በውጤት ምዘና ዙሪያ ለተቋሙ የስራ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። ለአመራሮቹ እና ባለሙያዎቹ አቅጣጫ የተሰጠበትን ስልጠና የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌጡ (ዶ/ር) እና ኮሚሽነር ብሌን ገ/መድህን ተገኝተው ሰጥተዋል። ኮሚሽነሮቹ ስራ አመራሮችና ባለሙያዎች በተቀናጀ ሁኔታ በቀሪ አስር ወራት የኮሚሽኑን ስራ እንዴት ማቀላጠፍ እንዳለባቸው […]